banner

በኮዬ ፈጬ በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው “ከንረቢ ጫላ” ሆቴልና መዝናኛ ለምርቃት ተዘጋጀ

​
#FastMereja I በኮይ ፈጬ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የመዝናኛ ቦታዎች እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል፣ በ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው “ከንረቢ ጫላ” የተሰኘው ዘመናዊ ሆቴልና መዝናኛ ተጠናቆ ለምርቃት መዘጋጀቱን ባለቤቱ አቶ ጫላ ቱፋ (አባ ገዳ ጫላ ቱፋ) አስታወቁ።

ባለቤቱ ቀደም ሲል በአርሶ አደርነትና በተለያዩ የንግድ ስራዎች ተሰማርተው ሲሰሩ እንደነበር ገልጸው፤ ከእርሻ ስራ ጎን ለጎን በዶሮ፣ እንቁላል፣ በግ እና ከብት እርባታና ንግድ በመሳተፍ ለአሁኑ ስኬት መብቃታቸውን ተናግረዋል። “ከንረቢ ጫላ” ማለት በኦሮምኛ “የእግዚአብሔር ይበልጣል” የሚል ፍቺ ያለው ሲሆን፣ የህንፃው ግንባታ ከአንድ ዓመት በፊት ተጀምሮ በፍጥነት መጠናቀቁ ተገልጿል።

​ህንፃው በቀጣይ እስከ 9 ፎቅ ለማሳደግ የታቀደ ሲሆን፣ በውስጡ ከ60 በላይ ዘመናዊ የመኝታ ክፍሎችን፣ የVIP እና VVIP አገልግሎቶችን እንዲሁም የመመገቢያ አዳራሾችን ያካተተ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከ60 በላይ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል አስተማማኝ የመሬት ስር (ግራውንድ) ፓርኪንግ እና የጥበቃ ስርዓት የተዘጋጀለት ሲሆን፣ በሆቴሉ የሚቀርቡት እንደ ስጋ እና እንጀራ ያሉ ምግቦች ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው እርሻ እና በአዳማ በሚገኘው የበረት ማደለቢያ ከደለቡ ከብቶች የሚዘጋጁ በመሆናቸው 100% ኦርጋኒክ እንደሆኑ ተገልጿል።

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በዚህ ቅርንጫፍ ለ150 ዜጎች፣ በሌላኛው ቅርንጫፍ ደግሞ ከ50 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች (በአጠቃላይ ከ200 በላይ ለሆኑ ዜጎች) የቋሚ ስራ እድል መፍጠሩን የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል።

​የሆቴሉ የምርቃት ስነ-ስርዓት ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም ለተከታታይ 7 ቀናት በደመቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ አቶ ጫላ ገልጸው፤ ለከተማው ማህበረሰብ፣ ለዘመድ ወዳጆችና ለደንበኞች ጥሪ አስተላልፈዋል። የሆቴሉ አድራሻ ከኮዬ አደባባይ ወደ ቱሉ ዲምቱ በሚወስደው መንገድ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ፊት ለፊት ይገኛል።

​ባለቤቱ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ለመወጣት በኮዬ አካባቢ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሁለት የንጹህ መጠጥ ውሃ ጉድጓዶችን አስቆፍረው ለአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጋቸውንም አክለው ገልጸዋል። በቀጣይም የመንግስትን የኢንቨስትመንት ፈቃድ በማስፋፋት ለህፃናት መጫወቻ ቦታዎችን፣ የመዋኛ ገንዳዎችን፣ የባህል ቤቶችን እና ሰፊ የህዝብ መዝናኛዎችን የመገንባት ትልቅ እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

#ቢዝነስ





5 comments

Elias Bukayo Saka Arsenal October 29, 2026 - 2:38 pm

ከንረቢ ጫላ🤔

Reply
Frew Abebe Hm October 29, 2026 - 2:38 pm

ሆቴሎች መዝናኛ ያካተቱ መሆን ዘመናዊነት ነው

Reply
Dawit Ilma Abbaa Raammatte October 29, 2026 - 2:40 pm

እሴይ !

Reply
እዝል ሚዲያ - Ezil midia October 29, 2026 - 2:40 pm

ከህዝብ በተዘረፈ ብር ለእነ ጫላ የዛፍ ማምለኪያ ተሰራ

Reply
Sile Sangawe October 29, 2026 - 2:40 pm

300ሚልየን ስንት ሆቴል ይከፍታል አልበዛም

Reply

Leave a Comment