banner

ኢትዮ አዛሄል ሪል እስቴት የመጀመሪያ ፕሮጀክቱን አስረከበ

#FastMereja I ኢትዮ አዛሄል ሪል እስቴት በመገናኛ አካባቢ ያስገነባውን ባለ 16 ወለል ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት አጠናቆ ለደንበኞቹ በይፋ አስረከበ።

ድርጅቱ ዛሬ ሕዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም በሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ የተረከበው ይህ ሕንፃ በእያንዳንዱ ወለል አራት አፓርትመንቶችን የያዘ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 64 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን አካቷል።

የመጀመሪያውን ፕሮጀክት በስኬት ማጠናቀቁን ተከትሎም፣ ኢትዮ አዛሄል ሪል እስቴት በቦሌ ፒኮክ አካባቢ አዲስ ባለ 23 ወለል ዘመናዊ አፓርትመንት ግንባታ በይፋ መጀመሩን አብስሯል። አዲሱ ፕሮጀክት የተሻለ የዲዛይን ጥራት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ምቹ የመኖሪያ አማራጮችን ይዞ እንደሚቀርብ ተገልጿል።





Leave a Comment