0
#FastMereja I የዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) በ2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2025) የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ ምክንያት ለሞሮኮ ተሰጥቶ የነበረውን የሻምፒዮንነት ክብር በመሻር፣ ሴኔጋል የውድድሩ አሸናፊ መሆኗን በይፋ ወሰነ።
በፍጻሜው ጨዋታ ሴኔጋል ሞሮኮን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ብታሸንፍም፣ በጨዋታው ወቅት በተሰጠ የፍጹም ቅጣት ምት ውሳኔ ላይ ተቃውሞ በማሰማት የሴኔጋል ተጫዋቾች ሜዳ ለቅቀው በመውጣታቸው ምክንያት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ዋንጫውን ለሞሮኮ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የካፍን ውሳኔ በመቀልበስ የ2025ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ክብር ለሴኔጋል እንዲመለስ በይፋ መወሰኑን አስታውቋል።
