banner

«ዘመን ተዋህዶ ኤክስፖ» በኤግዚብሽን ማዕከል ተከፈተ

‹‹ዘመን ተዋሕዶ ኤክስፖ›› ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ዛሬ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ተከፈተ። ከሐምሌ 12 አስከ 21/2016 ዓ.ም ለተከታታይ 10 ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ይህ የተዋሕዶ ኤክስፖ ከተለመደው የኤግዚቢሽን እና ባዛር አቀራረብ እጅግ አነስተኛ በሆነ የመገቢያ ዋጋ፣ የህብረተሰቡን አቅም ያማከሉ ምርት እና አገልገሎቶችን በማቅረብ በዘላቂነት በመስራት የህብረተሰቡ የኑሮ ገብቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝበት የገበያ አማራጭ እንደሆነ ተገልጿል።

በኤግዚብሽኑ በምሽት መርሃ ግብር 10 ታላላቅ ጉባኤዎች በደማቅ ሁኔታ ደቀርባል። በቂ የመኪና ማቆሚያ እና ልዩ የህጻናት ማቆያ እንደተዘጋጀ ተገልጿል።

ይህን የመጀመሪያ የዘመን ተዋሕድ ኤክስፖ ማርኮናል ኢንተርቴመንት እና ኤቨንት፣ ከሎዛ ኦርቶድክሳዊ ኹነቶች ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ነው።

Leave a Comment