በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል፣ በጉራጌ ዞን፣ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ11 ዓመት እድሜ ያላትን የአብራኩ ክፋይ የሆነች ልጁን የደፈረው አባት ውሳኔ እንደተላለፈበት የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሽ ሙሂዲን ወራቄ የግል ተበዳይ (ልጁ) ያለ እድሜዋ በአዲስ አበባ ከተማ በሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረ ሲሆን በኃላም ፤ በቤተሰቡ መበተን ምክንያት በብቸኝነት የሚኖረዉን አባቷ ለመደገፍ ወደ ከዊሶ ወደ ተባለው መንደር መመለሷን የገለፀው ፖሊስ ተከሳሹ ጋብቻ እየመሰረተ ሲፈታ ከሶስት ጊዜ በላይ ትዳር መስርቶ ፍቺ የፈፀመ ሲሆን የደረሱ ልጆቹንም ድሮ የልጅ ልጅ ለማየት በቅቷልም ነዉ ያለው።
ከአዲስ አበባ የተመለሰችውና ” አባቴን ትቼ የትም አልሄድም ” ስትል ከወላጅ አባቷ መኖር የጀመረችዉ ታዳጊ በተደጋጋሚ በገዛ አባቷ የተደፈረች ሲሆን አንድ ቀን በወላጅ አባቷ ጭካኔና የነዉረኝነት ባህሪ የደረሰባትን በደል ሁሉ ለወላጅ እናቷ ትናገራለች።
አንጀቷ የበገነው እናትም ወደ ወረዳዉ ሴቶች ጉዳይ ጽህፈት ቤት አቅንታ ሰዉየዉ ለፍርድ ይቀርብ ዘንድ እገዛ እንዲደረግልኝ ስትል አቤቱታ በማሰማቷ ክስ ሊመሰረት ችሏል።
ጉዳዩን ሲመከት የቆየው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ በማለት በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደወሰነበት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቁሟል።