የኮሪያ የህክምና ቡድን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልብ ህመም ችግር ላለባቸው ህጻናት ይሰጠው የነበረውን የነጻ የህክምና አገልግሎት አጠናቀቀ ፡፡
የኮሪያ የህክምና ቡድን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአመት ሁለት ግዜ በመምጣት ሲወለዱ ከፍተኛ የልብ የህመም ችግር ያለባቸውን ህጻናትን ህክምና በመስጠት የስድስት ቀን ቆይታውን አንዳጠናቀቀ የልብ ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስትና የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ልብ ቀዶ ህክምና ከፍል ሓላፊ ዶ/ር አበበ በዛብህ ተናገሩ ፡፡
የህክምና ቡድኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመጣው የተለያዩ ለህክምና አገልግሎት ላይ ሊውሉ የሚችሉ የህክምና ግበዐቶችን ይዞ ሲሆን እነዚህን ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በመጠቀም የልብ የቀዶ ህክምና አገልግሎቱን በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል ፡፡
የኮሪያ የክምና ቡድኑን የሚመሩት ፕሮፊሰር ጄኤ ጉን ኩዋክ (Professor Jae Gun Kuak ) በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከፍተኛና የተሳካ የልብ ቀዶ ህክምና ማድረጋቸው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልብ ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ( ዩኒት ) ክፍል ሓላፊ ዶ/ር አበበ በዛብህ ተናግረዋል ፡፡

ዶ/ር አበበ በዛብህ አንደተናሩት የልብ ቀዶ ህክምና ቡድኑ በአገር ውስጥ ሊሰጡ የማይችሉና ከፍተኛ ወጪ ሊጠይቁ የሚችሉ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በልብ ህክምና ለሚሰቃዩ ህጻናት ህክምናው አንደተደረገላቸውና ህክምናው ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ የሚጠይቅ በመሆኑ ከኮሪያ የልብ የህክምና ቡድን እና ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ጋር በጋራ ህክምናው አንደተሰጣቸው ገልጸዋል ፡፡
አንደ ዶ/ር አበበ በዛብህ ገለጻ ህክምናው የተሰጠው የልብ ቀዶ ህክምና በማድረግና በደምስር በኩል ካቲተር ባመስገባት ህክምናው የተከናወነ አንደሆነና ከነዚህም መካከል አስራአንዱ ህጻናት በልብ ቀዶ ህክምና ሶስቱ በደም ስር ውስጥ ካቲተር በማስገባት ህክምናው አንደተደረገላቸው ተናግረዋል ፡፡
የኮሪያ የህክምና ቡድን ላለፉት ዘጠኝ አመታት ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በተደረገ የህክምና የጋራ የመግባቢያ ስምምነት በአገር ውስጥ ሊሰጡ የማይችሉትን ህክምናዎች እየሰጡ አንደሚገኙ ተናግረዋል ፡፡
የኮሪያ የህክምና ቡድን ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቡድን ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ በመቀጠል ከህክምና ቡድኑ ሙያዊ የህክምና ልምድና እውቀት በመቅሰም ስልጠናዎችንና የአውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን በውሰድ የመማር ማስተማር ፤ የምርምርና የማህበራዊ የጤና አገልግሎት ላይ የበለጠ የተሸለ ለውጥ ለማምጣት አብረው አንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡
ዶ/ር አበበ በዛብህ አንደተናገሩት የኮሪያ የህክምና ቡድን ወደ አገራችን ኢትዮጵያ በመምጣት የሰጡት የህክምና አገልግሎት ከአገር ውጭ ሄደው ሊታከሙ የማይችሉትን ህጻናት ከሞት የታደገና ቤተሰቦቻቸው በሚሊዮኖች የሚያወጡትን ወጪዎች ያስቀረና አንዲሁም ለቤተሰቦቻቸውን አፎይታና አርካታ አንዲያገኙ ያደረገ አንደሆነ ገልጸዋል ፡፡
የልብ ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር አበበ በዛብህ አያይዘው አንደተናገሩት ኮሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ረዘም ላሉ አመታቶች ነበራቸውን የጋራ ወዳጅነት ጭምር በማስታወስ የኮሪያ የልብ ቀዶ ህክምና ቡድን ጋር ይህን ግንኙነት በማጠናከራቸው ምክንያት የህክምና ቡድኑ በራሳቸው ወጪ ለህክምና የሚያስፈልገውን የክምና ግብዐቶችን ወጪዎች በመሸፈን የበለጠ ወዳጅነታቸውን በመሳየታቸው መደሰታቸውን የህክምናውን የሚመሩትን ፕሮፊሰር ጄኤ ጉን ኩዋክንና የህክምና ቡድናቸውን አመስግነዋል ፡፡

አንደ ዶ/ር አበበ በዛብህ ገለጻ የህክምና ቡድኑ የተለየ የሚያደርገው በማላዊ በመንግስትና በግል ህክምና ተቋም በአገሩ ክትትል ሲያደርግ የነበረውን የሁለት አመት ከስድስት ወር ህጻን ( Kasunda Leonard ) ካሱንዳ ሊዮናርድ ወደ ኢትጵያ በመምጣት በኮሪያ የህክምና ቡድንና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ሀኪሞች ቡድን የልብ ቀዶ ህክምና ተሰርቶለት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንደሚገኝና ከሁለት ቀን በኋላ ወደ አገሩ ማላዊ አንደሚለስ ተናግረዋል ፡፡
የኮሪያ የልብ ቀዶ ህክምና ቡድን የልብህክምና ተልኮውን በማጠናቀቁ ዛሬ ማታ ወደ አገራቸው ኮሪያ አንደሚመለሱ ተናግረዋል ፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለኮሪያ የህክምና ቡድን የምስጋና ሰርተፍኬት ከፕሮፌሰር አንዱአለም ደነቀ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስክዩቲፍ ዳይሬከተርና የልብና የደረት ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስ ዶ/ር አበበ በዛብህ አጅ ተበርክቶላቸዋል ፡፡