banner

የአራዳ መጠጥ አምራች የሆነው ኮማሪ ቢቨሬጅ የአለም አቀፍ የምርት ጥራት ሞንድ ሰሌክሽን የወርቅ ተሸላሚ መሆኑን ገለፀ

የአራዳ መጠጥ አምራች የሆነው ኮማሪ ቤቨሬጅ የአራዳ ሎሚ ምርት በ63ኛው የአለም አቀፍ የሞንድ ሰሌክሽን የምርት ጥራት ሽልማት ማሸነፉን ዛሬ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

አቶ ክፍለዮሐንስ አበበ የኮማሪ ቢቨሬጅ ዋና ስራ አስኪያጅ ናቸው ምርቶችን ጥራት በጥንቃቄ በመገምገም አሸናፊ ብራንዶችን እውቅና በሚሰጠው ሞንድ ሰሌክሽን የአራዳ ሎሚ ምርት የ2024 የወርቅ ሽልማት አሸናፊ መሆኑን በሰጡት ጋዜጣዊ ላይ ገልጿል ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዛሬው ውሎ በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ተቋማት ከገበያ ፉክክር ባሻገር በቅርበት ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ በጋራ የመከሩ ሲሆን የቤቨሬጅ አምራች ዘርፍ ወቅታዊ የቢዝነስ ምህዳር፣ መልካም ዕድሎችን እና መጻኢ ዕጣ ፈንታ ዙሪያ ከተለያዩ የቤቨሬጅ አምራች ተወካዮች ጋር የፓናል ውይይት ተደርጓል።

የሚጣሉ ታክሶች፣ የትራንስፖርት ዋጋ፣ የጥሬ እቃ አቅርቦት የውጪ ምንዛሬ ለዘርፉ አለማደግ እንቅፋት እንደሆኑ በመድረኩ ላይ ተነግሯል።

ለዛሬው የውይይት መርሐግብር መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የምሥጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

Leave a Comment