banner

በፓሪስ ኦሎምፒክ በኢቢሲ የስፖርት ተንታኝ ለነበሩት ኢንስትራክትር መሰረት መንግስቱ እውቅና ተሰጠ

ኢንስትራክተር መሰረት መንግስቱ በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድሮች በኢቢሲ ስፖርት ቀጥታ ስርጭት ጥልቅ ሙያዊ ትንታኔ በመስጠት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዕውቅና ሰጥቷቸዋል።

ኢንስትራክትር መሰረት ላደረጉት ሙያዊ እገዛ ኢቢሲ እውቅና ከመስጠት ባለፈ በቋሚነት የተቋሙ የስፖርት ተንታኝ አድርጓቸው እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

Leave a Comment