banner

ዩኒማስ ማኑፋክቸሪንግ የኤክስፓርት ስታንዳርድ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ።

ዩኒማስ ማኑፉክቸሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በዘመናዊ እና በከፍተኛ ጥራት የተዘጋጁ የኤሌክትሪክ እቃዎችን በማምረት ላለፉት አስርት ዓመታት ለሀገር ውስጥ ገበያ ያቀረበ ሲሆን አሁን ደግሞ “ሀገሬ ጥራት ይገባታል” በሚል ርእስ የኤክስፓርት ስታንዳርድ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረቡን እና ወደ ውጭ ለመላክ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ዛሬ ነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ዩኒማስ ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ በእውቁ የፈጠራ ባለሙያ ስም የተሰየመ “ኤዲሰን” የሚባል የንግድ ምልክት በጥር ወር 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት አስመዝግቦ በኤዲሰን የንግድ ስምና ምልክት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የተለያዩ የኤሌክትሪክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም ለአስርት አመታት የቤት ውስጥ እና የኢንዱሰትሪ የመገልገያ እቃዎችን እያቀረበ ቆይቷል፡፡

ድርጅቱ ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል ለአብነት ያክል የተለያዩ ኃይል ቆጣቢ ኤልዲ መብራቶች፣ ብሬከሮች፣ ኤክስቴንሽን ሶኬቶች፣ ልቴጅ ሬጉሌተሮች የሚጠቀሱ ሲሆኑ ምርቶቹንም በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ የጥራት መስፈርቶች በማሟላት እያመረተ ይገኛል ተብሏል። በተጨማሪም የውጭ ባለሙያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስመጣት ሰራተኞችን እንዲሰለጥኑ እድል በማመቻቸት ብዛት ያላቸው ኢትዮጲያውያንን የሥራ እድል እንዲያገኙ እና የቴክኖሎጂ ሸግግርም እንዲሳለጥ አድርጓል፡፡

ዩኒማስ ኢንጂነሪንግ በአጭር ጊዜ በሀገር ውስጥ እየገጣጠማቸው የሚገኙ የኤሌክትሪካል እቃዎችን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ለማምረት ዓለም አቀፍ ልምድ ካለው አማካሪ ድርጅት ጋር ስምምነት ያደረገ ሲሆን ለኢትዮጵያ ኢንቨሰትመንት ኮሚሸን ፕሮፖዛል አቅርቦ የምርቶቹ አስፈላጊነት ላይ ጥልቅ ውይይት እና ማብራሪያ ቀርቦበት ያቀረብነው ፕሮፖዛል ከተገመገመ በኃላ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ 11647 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ ተፈቅዶልን አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በማሟላት ቦታውንም መረከቡን ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እያለ ጥራት ያለው ኤክስፓርት ስታንዳርድ ምርት በሀገራችን ለማምረት በቁርጠኝነት እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት አስፈላጊውን ማሽኖች ስመጥር ከሆኑ ኩባንያዎች ከጃፓን-ፓናሶኒክ SMT1 ከደቡብ ኮሪያ ሳምሰንግ production line ከጀርመን ቴድሪክ injection machine አና testing laboratory ሌሎችም ለማስመጣት ቅድመ ዝግጅት አድርጓል ተብሏል።

Leave a Comment