«ንግስት» የተሰኘ የነፍሰጡሮች የፋሽን ሾዉ ውድድር ከጤና ጥበቃ ሚንስትር ጋር በመተባበር መዘጋጀቱ ተገለፀ።
ታዋቂ ኤቨንትስ ለሀገራችን የመዝናኛ ኢንዱስትሪ በርካታ ኤቨንቶችን በማዘጋጀት ይታወቃል “ንግስት” የተሰኘው ይህ የውድድር መስከረም 11/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ዛሬ ነሃሴ 16/2016 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።
ፕሮግራሙ ለመውለድ የተዘጋጁ ነፍሰ ጡሮች በዲዛይነሮች በተዘጋጁ ቅንጡ አልባሳት የተዘጋጁላቸውን ልብሶች በመጠቀም ይበልጥ በእርግዝና ወቅት አሳሳቢ በሆኑት የነፍሰጡር አልባሳት ተውበው የሚታዩበት፤ ምቾትን ተጎናጽፈው ራሳቸውን የሚገልጹበት፣ ለተለያዩ ስሜቶች ተጋላጭ የሆነውን ይህንን የእርግዝና ጊዜ በተዝናኖት የሚያሳልፉበት፣ ባለቤቶቻቸዉ በሚጠየቁት የእርግዝና ነክ ጥያቄዎቸ አማካኝነት እየተዳኙ ተወዳድረው በርካታ አጓጊ ሽልማቶችን የሚያገኙበት እንደሆነ ተገልጿል።
አላማውን በሀገራችን በስፋት እየተስተዋለ ስለሚገኘው የእናቶች በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ህይወት ማለፍን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠርን ተነሳሽነት በማድረግ የተዘጋጀ ፕርግራም ነው ተብሏል።
በዛሬው እለትም በኢትዮጵያ የደም ባንክ በመገኘት የደም ልገሳ መረሃ ግብር ተከናውኗል።