አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በ2023/24 ሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን አብስሯል፡፡ በቀረበው ሪፖርት መሠረት ባሳለፍንው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡
በሒሳብ ዓመቱ ብር 232 ሚሊዮን አጠቃላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን በዓመቱ ውስጥ የነበረው የወጪ አፈፃመማችን 183 ሚሊዮን ብር በመሆኑ 47 ሚሊዮን ብር ማትረፍ ችለናል፡፡ ለተገኘው ትርፍ ተቋማችን የተገበራቸው የወጪ ቅነሳ ስትራቴጂዎች ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል።

የተቋማችን 95 ሺ በላይ ደንበኞች አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ብር 1.636 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከብር 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ለ8 ሺ 250 ደንበኞች አቅርቧል፤ የተሰጡ ብድሮች ለቤት ውስጥ ፍጆታ ብድር፣ ለቢዝነስ ማስፋፊያ፣ ለግብርና ብድር፣ ለቤትና ተሽከርካሪ ግዥ ብድር ለማኅበረሰቡ ተደራሽ አድርጓል፡፡
በ21 ሚሊዮን ብር ካፒታል ሥራ የጀመረ ይኸው ተቋም በአሁኑ ሰዓት የተከፈለ ካፒታል ብር 136 ሚሊዮን እንዲሁም ጠቅላላ የተቋሙ ሃብት ብር 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ደርሷል፡፡
ለዘንድሮው ውጤት መመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ ላበረከቱት ደንበኞች፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሠራተኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል።
በ2017 ሒሳብ ዓመትም ተቋማችን1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ አክሲዮኖችን ለሽያጭ ያቀረበ ሲሆን፣ 200 ሺ 052 ደንበኞችን በማፍራት 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የተቀማጭን ገንዘብ በመሰብሰብ ለ20,002 ደንበኞች 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ለደንበኞች ያቀርባል። እንዲሁም የአክሲዮን ትርፉን በአንድ ሺህ ብር፤ አምስት መቶ ብር ለማከፋፈል በትኩረት እሰራለሁ ብሏል።