የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሙስናን ለመቀነስ ትኩረት አድርጎ በመስራት ከከተማው 42 ተቋማት የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ በቀዳሚነት ተሸላሚ ሆነ
#FastMereja
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመቀነስ ትኩረት አድርጓ በመስራት መሻሻልን ያሳዩ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።
በዚሁ መሰረት ምዘና ከተደረገባቸው 42 የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ሙስና ለመቀነስ በመስራት እንዲሁም እርምጃ በመውሰድ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የአንደኝነት ደረጃ እውቅና ተሰጥቶታል።
ኤጀንሲው በበጀት ዓምቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከሌብነት እና ሙስና የፀዳ ለማድረግ የዲጂታል አገልግሎትን በ119 ወረዳዎች ላይ የተሟላ የማድረግ ፣ የኦዲት ስርዓት በመዘርጋት ፣የሰራተኛ የደንብ ልብስ እና ስነ-ምግባር መመርያ በማውጣት እንዲሁም ከ238 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ፣ ህገ-ወጥ ደላሎች ፣ ሃሰተኛ ሰነድ የያዙ ተገልጋዮች ላይ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።
በመርሃ-ግብሩ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተገኝተው እውቅናውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ሮቢ ተቀብለዋል።
