banner

“ችግኝ እንተክላለን ለመጪው ትውልድ እንሰራለን” ኤስ ሳራ ግሩፕ

የኤስ ሳራ ግሩፕ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ረ አብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረውን ‘’የአረንጓዴ አሻራ” ዘመቻ በማስቀጠል የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በሆለታ ከተማ አከናውኗል።

የድርጅቱና የሆለታ ከተማ አመራሮች እንዲሁም ሰርተኞችና የከተማዋ ነዋሪዎች በጋራ በመሆን ከ6ሺ በላይ ችግኞችን ተክለዋል።

ኤስ ሳራ ግሩፕ ላለፉት አምስት አመታት በተከታታይ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ያከናወነ ሲሆን በአጠቃላይ ከአርባ ሺህ በላይ ችግኞችን ተክሎ ከዘጠና በመቶ በላይ ጸድቀው የአከባቢውን ስነ ምህዳርና ግጽታ እስክመቀየር ያስቻለ ስራ ተሰርቷል።

ኤስ ሳራ ግሩፕ ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ለህዳሴ ግድብ፣ ለገበታ ለሃገር፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች፣ ለአቅመ ደካሞችና በተለያይዩ ግዚያት በመንግስትና ህዝብ ለሚቀርብለት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ እስካሁን ከ አንድ መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ብር በላይ እርዳታ አድርጓል።

ኤስ ሳራ ግሩፕ አሁን ላይ ኤስ ሳራ ኮፊ ኤክስፖርት፣ አፍሪካ ውሃ፣ አፍሪካ ብረት፣ ኤስ ዲ ጨውን ጨምሮ ከ16 በላይ ኩባንያዎችን በስሩ እያስተዳደረ ይገኛል።





Leave a Comment