banner

የ3 አመት ህፃን አስገድዶ የደፈረው የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈረደበት

#FastMereja
ጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ የግብረስጋ ድፍረት በደል የፈጸመው ተከሳሽ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተወስኗል።

ተከሳሽ አቶ ቱካ ቱጋሞ ዕድሜ 45 ስሆን በ1996ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 627(5) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የዲታ ወረዳ አቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የግብረስጋ ግንኙነት በመፈጸሙ ነሀሴ 5/ 2016ዓ.ም ዕሁድ ከቀኑ 9:00 የሚሆንበት ጊዜ በዲታ ወረዳ ዛዳ ከተማ ቀበሌ ልዩ መጠሪያው ሚሽዳ ቀጠና ተብሎ የሚጠራበት አከባቢ የ3አመት ልጅ የሆነችውን የግል ተበዳይ ህፃን ብርቱ ገነነ ዕድሜ ሦስት ዓመት የሆነችው ልጅ ከሌሎች ልጆች ጋር ከብቶችን በሚያግዱበት ቦታ ተከሳሽ አንቀላፍታለች በማለት አቅፎ ወደ ተበዳይ ወላጅ አባቷ ቤት ድረስ በማምጣት አስገድዶ በመድፈር የከባድ አካል እና ሥነ ልቦና ጉዳት ያደረሰባት በመሆኑ የፈፀመው በህፃን ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ አቅርቧል።

ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያሰረዳ ሲሆን ተከሳሽም ወንጀሉን ስላለመፈጸሙ ማስረጃ አቅርቦ ያላሰተባበለ በመሆኑ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ነሀሴ 22/2016 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እዲቀጣ ተወስኖበታል ሲል የዲታ ወረዳ መ/ኮሚዩኒኬሽን ነው የዘገበው።

10 comments

Umumarya Jm August 28, 2024 - 2:01 pm

ፈርደው ሞተዋል

Reply
Sultan Kebede August 28, 2024 - 2:02 pm

አይ እድሜ ልክ

Reply
Selam Mekonene August 28, 2024 - 2:02 pm

ፍትህ በግፍ ለሚደፈሩ ህፃናቶች😭

Reply
Beri Love Sime August 28, 2024 - 2:02 pm

Wusanewu biyanisim yihun kelelawu yishalalina mot bihon arp neber😭

Reply
Kibru Doge August 28, 2024 - 2:03 pm

እግዝዮ ማረን🙏
አሁንስ እንደዚህ አይነት ዜና በዛ😡
ኤር መንግስት ሆይ አስተማሪ እርምጃዎች በህገመንግስቱ ላይ ልካተቱ ይገባልና አስቡበት🙏

Reply
Wegayehu Muluneh August 28, 2024 - 2:04 pm

በተለይ አስገድዶ መድፈርን በተመለከተ የሚሰሩ ወንጀሎች በድብቅ በመሆናቸው፣ በተቃራኒው ደግሞ ህጉ የሰው ምስክር የሚፈልግ በመሆኑ የበዙት ፍትህ ሳያገኙ ቀርተዋል። ህጉ ሌላ አይነት የምርመራ መንገድ መከተል አለበት። ይሄን ግን እዛው እስር ቤት ወዬ ወዬ ይበሉት።

Reply
Highroof Abadulla August 28, 2024 - 2:04 pm

ፊትሕ ለጎንደሯ ህፃን ፌበን

Reply
Ashu F Marye August 28, 2024 - 2:04 pm

አይይ ኢትዮጲያ በአንድ ሀገር ተመሳሳይ ወንጀል የተለያየ ፍርድ

Reply
Wėnde Mulat August 28, 2024 - 2:04 pm

ኧረ በፈጣሪ ስም ምንድነው የምንሰማው ወዴት እየሄድን ነው 😭 ኧረ ይሄ ነገር በጣም እየበዛ ነው ዝም ተባሉኮ።

Reply
Kedst AIemnew August 28, 2024 - 2:06 pm

ህግ አልባ ሀገር ፈርደው ሙተዋል

Reply

Leave a Comment