0
#FastMereja
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ማንነትን መሠረት ያደረገ ነው በተባለ ጥቃት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ተገደሉ ፡፡ ግድያው የተፈጸመው በልዩ ወረዳው ዲዳ ሀሊቦ በተባለ ቀበሌ ውስጥ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
የሟቾቹ የቅርብ ቤተሰብ አባል መሆናቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩትና አቶ ሁሴን ለመንጎ የተባሉ የዲዳ ሀሊቦ ቀበሌ ነዋሪ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ባለፈው ማክሰኞ የፈጸሙት ሟቾቹ ሌሊት በተኙበት የተኩስ እሩምታ በመክፈት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በጥይት ከተመቱት አሥራ አንድ ሰዎች መካከል የሰባቱ ህይወት ወዲያ ማለፉን የጠቀሱት የዓይን አማኙ “ ከሟቾቹ መካከል አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ ሁለቱ ህጻናት ናቸው ፡፡ ቀብራቸውም ትናንት ሐሙስ ተከናውኗል “ ብለዋል ፡፡
ጥቃቱ ማንነትን መሠረት ያደረገ ፣ ዘግናኝና ታቅዶ በህጻናትና ሴቶች ላይ የተፈጸመው መሆኑን የጠቀሱት የሟች ቤተሰብ አሁን ላይ በጥቃቱ የቆሰሉት አራት ሰዎችን ደግሞ በወራቤ ሆስፒታል አስገብተናል ” ብለዋል፡ ሲል ዶቼ ቬለ ነው የዘገበው።

5 comments
አይ ሰው 😔ማርያምን ግን ለምን ሰውነቱን ረሳነው?
ለሄቨን #ፍትህ ስትጠይቁ የነበረችሁ ደጋግ ኢትዮጵያን ዬት ነው ያለችሁት ? በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማረቆ ልዩ ወረደ እንደ ሄቨን ያሉ ምንም የማያውቁ ጨቅላ ህፃናት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ወንበዴ ቡድን እየተረሸኑ ይገኛሉ ።
#ደጋግ ኢትዮጵያን #ለማረቆ ህፃናትና እናቶች #ፍትህ ጠይቁ ።
#ፍትህ ለማረቆ ህፃናት !
#ፍትህ ለማረቆ እናቶች !
#ፍትህ #ፍትህ
#ፍትህ
#ፍትህ
ፈጣር ይቅር ይበለን
ጉራጌም ተበላሸ😭
መርጦ ላልተወለደው በዚ ልክ መጠላላት ያሳዝናል