#FastMereja
ጆርዳን ቢዉቲ አካዳሚ የኢትዮጵያ ሜካፕ አርቲስቶች (EMA) የተሰኘ የዉድድር መርሀ ግብር በማዘጋጀት በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉ ባለሙያዎችን እዉቅና እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ዛሬ 25/2016 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
ይህ ልዩ የሜካፕ አርቲስቶች ሽልማት ዉድድር በአባይ ቲቪ ላይ የሚተላለፍ ሲሆን አዝናኝ እና ተወዳጅ የቲቪ ፕሮግራም እንደሚሆን እርግጠኞች ነን ሰሉ አዘጋጆቹ ተናግሯል።
የኢትዮጵያ ሜካፕ አርቲስት አዋርድ (EMA Award) በኢትዮጵያ የመጀመርያው የገፅ ቅብ ውድድር እንደመሆኑ የውበት ኢንዱስትሪውን ከፍ ያደርጋል ሲሉ የአካዳሚዉ መስራች የሜካፕ አርቲስት እና መምህር በሆነዉ አቶ እስራኤል ብርሀኑ (ጆርዳን) ተናግሯል።
አዳዲስ የሜካፕ ባለሙያዎችን ከተመልካች ጋር በማስተዋወቅ የስራ እድሎችን ይፈጥራል የተባለው የሽልማት ውድድሩ በከፍተኛ ድምፅ እና ምርጫ ሂደት የላቀ የስነጥበብ ፣ የቴክኒክ ክህሎት እና የኢትዮጵያን የውበት ኢንዱስትሪን ለማራመድ ቁርጠኝነትን ያሳዩ ሜካፕ ባለሙያዎችን በመለየት እዉቅናን እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ውድድር ለ13 ሳምንት የሚዘልቅ ሲሆን ዳኝነቱም በየውድድሩ በተለያየ የዳኝነት መንገድ ማለትም አሸናፊዎች በኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ሰዎች እንዲሁም በህዝብ ምርጫ ይመረጣሉ።
አሸናፊ ለሆኑ ባለሙያዎች ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት እና የዋንጫ ስጦታ እንዲሁም ከሀገር ውጭ የአጭር ጊዜ የሜካፕ ስራ ስልጠና (Masterclass) እንዲሁም የነፃ የትምህርት እድል የማግኘት እድሎችን ያስገኛል።
ጆርዳን ቢዉቲ አካዳሚ የሜካፕ አርቲስት እና መምህር በሆነዉ አቶ እስራኤል ብርሀኑ (ጆርዳን) በ2013 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡
📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ





3 comments
Samri Mati
ኦ አዋርድ ቀን ወጣለት!
ይቺ ልጅ ግን ከግሩም ከስር ከስር ለምንድነው ምትኖረው😁😁😁