0
ነፍሳችንን በእግዚአብሔር ፊት ልናከብራት እነሆ የእናቱ የእናታችን የመታሰቢያ በዓል ደረሰልን። በልዩ መንበሯ ሃገሯ ግሸን ማማሯ ብሎ ዘማሪው ያወደሳት ፣ ካህናት አባቶች መነኮሳት እናቶች ለበረከት የሚገናኙባት ታላቋ ምድር ግሸን ደርበ ከርቤ።
የክረምቱን ጭጋግ የወቅቱን ፈተና አሳልፎን ለምስጋና ያበቃንን እናመሰግን ዘንድ ልዩ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ግሸን ደርበ ከርቤ ተዘጋጅቷል።
በዓለ መስቀሉን ከመስቀሉ ቦታ የምናከብርበት ኦርቶዶክሳዊ ጉዞ ለኦርቶዶክሳውያን።
በጉዞአችን ፦ የሐይቅ ገዳማትን ጨምሮ ሌሎችን ገዳማትን የምንሳለምበት በረከተ ከእግዚአብሔርን አግኝተን ምስጋናችንን አድርሰን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተን የምንመለስበት ጉዞ ይመዝገቡ።
የጉዞ መነሻ ቀን፦ መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የጉዞ መመለሻ ቀን፦ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም
የጉዞ ዋጋ፦መአድ ፣ ትራንስፖርት እና ማረፊያን ጨምሮ 5,500 ብር ብቻ
ለበለጠ መረጃ ፦0938944444 ወይም 0964402728
ኑ በስሙ ተሰባስበን በመካከላችን እግዚአብሔርን አኑረን እናቱ እናታችንን እናመስግን።
አዘጋጅ:-ማኅበር ቁስቋም
