#FastMereja
ትንሿ ከተማ ከዜሮ እድሜ እስከ ሰባተ ዓመት ሕጻናት ያሉ ልጆችን በኢትዮጲያ የመጀመሪያ የሆነውን የልጆችን የወደፊት ማንነት የሚገነባ የሙያና እየተጫወቱ የአይምሮ ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያገኙበት የህፃናት መዝናኛ በላፍቶ ሞል ግራውንድ ውስጥ የልጆች ከተማ /Tiny Town/መከፈቱ ተገለጸ።
ትንሿ ከተማ ኢንተርቴይመንት መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አስናቀች ንጉሴ ማዕከሉን መከፈት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት ፣ ልጆች ከስክሪን እርቀው ጤናማ ግንኙነት ከቤተሰቦቻቸውና ከሌሎች ህፃናት ጋር ማድረግ እንዲችሉ የሚያግዝና የሚያስተምር በጣም ውብና ንፁህ የህፃናት ከተማ ከተሟላ እንክብካቤና ጥንቃቄ ጋር የተገነባው ከተማ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ህፃናቱ ወደ ትንሿ ከተማ ሲመጡ የመናገር ችሎታቸውን ማዳበር ፣ ከሌሎች ልጆች ጋር አንድ ላይ መጫወት ፣ በራሳቸው ችግርን መፍታት ፣ነገሮችን አብላልቶ ማሰብ ፣ በራስ መተማመን ችሎታን ማዳበር ፣ መሆን የሚፈልጉትን ህልም ማግኘት ፣ ተሰጦዋቸውን የሚያወጡበት ዕድል ማግኘት ፣ እንደ ልባቸው የሚጫወቱበት፣ ህግና ስነ ምግባርን የሚማሩበት ፤ አካላዊ እንቅስቃሴ እድገት ፣ አዕምሯዊ ዕድገትና እና ማህበራዊ ግንኙነት ሌሎችም ጥቅሞች ለልጆች ጠቃሚ እንዲሆኑ ታስበውና በጥናት መዘጋጀታቸውን ዶክተር አስናቀች ንጉሴ ገልጸዋል።




