#FastMereja
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በአፍሪካ የከተሞች ፎረም በመገኘት የከተማዋን ዝግጅት እና ተሳትፎን የተመለከተ ጉብኝት አደረጉ።
ከንቲባው በመድረኩ ተገኝተውም የሀዋሳ ልዑካን ቡድን
እያደረገ ያለውን ከተማዋን የማስተዋወቅ ሚና አድንቀዋል።
እንደ ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ ይህ መድረክ የአፍሪካ ከተሞችና ተቋማትን የእርስ በርስ ልምድ መለዋወጫ እና በጋራ አህጉራዊ የከተማ እድገትን ለማረጋገጥ ያስቻለም ነው።
በመድረኩ የሀዋሳ ዝግጅች ለአፍሪካ ከተሞች ያለውን ልምድ በሚገባ ማስተዋወቅ የቻለ እንደሆነም ነው የገለፁት።
ሀዋሳ ያላትን ከተማን የማስተዋወቅ ልምድ ተጠቅማ ከሌሎች ያደጉ ከተሞች ጋር እኩል ተወዳዳሪ የሚያደርጋትን ልዩ ዝግጅች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይዛ ስለመቅረቧም አያይዘው ገልፀዋል።
ሀዋሳ በስራ ላይ ነች፣ እየሰራችም ተገኛለች፣ በጥረት ያላትን እምቅ የማደግ አቅም ተጠቅማ ጉዞዋን ማስቀጠል እንደምትችል የገለፁት ከንቲባው ለዚህም የከተማዋ ማህበረሰብ በጋራ ሀላፊነቱን በሚገባ እንዲወጣ ጠይቀዋል።
ከተማዋ በመድረኩ ከሌሎች የአፍሪካ ከተሞች በቂ ልምድ ያገኘችበት እንደሆነ የተናገሩት ከንቲባው እኚህ ልምድና ተሞክሮዎች ይበልጥ በከተማ ልማት ፅንሰ ሀሳብ በመታገዝ ከዳር ለማድረስ በቀጣይ ይሰራልም ብለዋል።
በከተማዋ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተጠና መልኩ እና በተቀናጀ የልማት አካሄድ እየተከናወኑ ስለመገኘታቸው ያስረዱት ከንቲባው ለዚህም አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ በመጠቆም ነው ያመላከቱት።




1 comment
የወገን ያለህ! የህፍትህ ያለህ! የመንግስት ያለህ!
ይህ ከታች የተቀመጠው መልዕክት እኛ የኒያላ ኢንሹራንስ ኩባንያ ሰራተኞች በአዋጅ ለሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካል (ብሔራዊ ባንክ) ያሳወቅንበት አቤቱታ ነው። ስለሆነም ይህንን ለሚመለከተው የህግ አካል እንዲደርስ ቀና ትብብራችሁን እንሻለን ።
ለ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ
ኢንሹራንስ ሱፓርቪዥን ዳይሮክቴሬት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ:- ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሃብት ምዝበራን እና የመልካም አስተዳደር ችግርን ይመለከታል
እንደሚታወቀው ኒያላ ኢንሹራንስ ኩባንያ በሃገሪቱ ካሉ በቢሄራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝተው በስራ ላይ ካሉ 17 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይመደባል።
ይሁንና ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር እና ውንብድና በኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች በተደጋጋሚ እየተፈፀመ የህዝብ ሃብት እና
ንብረት በማን አለብኝነት እየተመዘበረ ይገኛል።ለዚሁ ማሳያ ይሆን ዘንድ የሚከተሉትን አንኩዋር አንኩዋር ጉዳዩች እንደሚከተው ቀርቧል
፩.ባሳለፍነው የበጀት አመት ብቻ የቢሄራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SB/46/2018 ለኩባንያው የቦርድ አባላት (Directors) በአመት ሊከፈል የሚችል ቦነስ ከ 150 ሽህ ብር መብለጥ የለበትም ብሎ ቢደነግግም ይህን መመሪያ በሚፃረር መልኩ ከ 6 ሚልየን ብር በላይ በቦነስ ስም ለኩባንያው ቦርድ አባል እንዲከፈል ተደርጓል (የኩባንያው አመታዊ የኦዲት ሪፓርት ኮፒ ተያይዟል)።
፪.በ አሳለፍነው በጀት አመት ማለትም (እኤአ 2022/23) ብቻ የኩባንያው ቦርድ ፈቅዷል በሚል የኩባንያውን ካፒታል እንዲሁም የተፈቀደ የስራ ዘርፍ ባላገናዘበ መልኩ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሃብት ማለትም ከ 100 ሚልየን ብር በላይ በዝቅተኛ ወለድ የረጅም ግዜ ብድር ብዙሃኑን ሰራተኛ ባገለለ መልኩ ከ 34 ላልበለጡ ጢቂት ሰራተኞች ብቻ ምንም አይነት ወጥነት በሌለው አግባብ ከፍተኛ አመራሮች እስከ የበታች ሰራተኛች (ሾፌሮች እና የጠቅላላ አገልግሎት ሰራተኞች)እንዲከፋፈል ተደርጓል።ለምሳሌ ከፍተኛ ብድር ከወሰዱት መካከል ስራ አስፈፃሚው ብር 9.9 ሚልዬን፣ የፋይናንስ ም/ስራ አስፈፃሚ ብር 5 ሚልዬን ፣ የካሳ ም/ስራ አስፈፃሚ ብር 4.4 ሚልዬን….ወዘተ ይገኙበታል። ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች የ100 ሚልዬን ብድሩን ከወሰዱ በኋላ ገንዘቡ አልቋል ቀሪው ሰራተኛ የሚወስደው ብድሩን የወሰዱት ሲመልሱ ነው በሚል ከፍተኛ የህዝብ ሃብት ለጥቂት የጥቅም ተጋሪዎቻቸው እንዲከፋፈል ተደርጓል።
፫.የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ በየአመቱ ከሚከፈላቸው የ 3% የትርፍ ድርሻ በተጨማሪ የኩባንያው ንብረት የሆነ አሁናዊ ግምቱ 4 ሚልዬን የሚገመት Hyundai Tuscon መኪና የባለቤትነት ሊብሬ ወደ ግል ንብረት ማለትም ወደ ኮድ2 C ***02 AA. እንዲዞር ተደርጎ መኪናውን ኩባንያው ለድርጅቱ ስራ ከመደበላቸው ሁለት የV8 መኪኖች በተጨማሪ ይህንኑ መኪና ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ ይገኛል።
፬.በኩባንያው ውስጥ በተንሰራፋው ስርአት አልበኝነት እና ማን አለብኝነት ጥቂት የስራ አመራሮች ኩባንያው የጣለባቸውን ሃላፊነት ችላ በማለት ሰራተኞችን በማንነታችን ብቻ ከደረጃ እና ደመወዝ ዝቅ እንዲሉ እንዲሁም ለጥቅም ተጋሪዎቸው እና በማንነት ለሚመስሉኣቸው ጢቂት ሰራተኞች በማዳላት ኩባንያው ለድርጅቱ ሰራተኞ ከሚሰጠው ጥቅማ ጥቅሞች ፣ ልዩ ልዩ የስራ ላይ ስልጠናዎች እና የትምህርት እድሎች፣ አመታዊ የደመወዝ እርከን ጭማሪ፣ የደረጃ እድገት፣ ወዘተ ተጠቃሚ እንዳንሆን ሆን ተብሎ ከፍተኛ የሆነ መገለል እና መድልኦ እየደረሰብን እንገኛለን።
፭.ኩባንያው እያስገነባ ያለው ባለ 18 ፎቅ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ (ህንፃው ቦሌ ከደንበል ህንፃ ፊት ለፊት ወይም ሸዋ ዳቦ አካባቢ ይገኛል) በብር 832 ሚልዬን ከቻይናው ኮንትራክተር (China WU Yi) ጋር ውል ገብቶ ሙሉ የ Structure ግንባታው ወደ 260 ሚልየን ብር ወጭ ያለቀ ቢሆን ለቀሪው የፊንሽንግ ስራ ውሉ እንዲድተካከል ተደርጎል።በዚህም መሰረት ለቀሪ የፊንሽንግ ስራ ውል የተገባለት ሂሳብ ወደ ከ2.498 ቢልዬን ብር በላይ ነው ይህም የጠቅላላ ወጭውን ማለትም የ832 ሚልዬን ብር ሶስት እጥፍ ያሆናል።
በተጨማሪም እነኝሁ የስራ ሃላፊዎች የስራ ሃላፊነታቸውን ተገን በማድረግ ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ፀያፍ ስድቦች በአደባባይ መሳደብ ፣ በስራ ባልደረቦች ፊት ማንቋሸ፣ አሉባልታ አሰራጭቶ ማሳደም፣ ለስራ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመደበቅ እና በመከልከል የመሳሰሉ ድሪጊቶች በመፈፀም የስራውን ከባቢ በመበከል ተረጋግተን ስራችንን በአግባቡ እንዳንሰራ እየተደረግን ተሳቀን እንገኛለን ።
በመሆኑም መስሪያቤታችሁ ከላይ የተገለፁትን የህግ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በውል ተመልክቶ መንግስትና ህዝብ የጣለበትን ከፍተኛ አደራ እንደሚወጣ እየተማመንን ባንካችሁ ለሚወስደው ማንኛውም እርምጃ በሙሉ ልብ ተባባሪ የምንሆን መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።
ከሰላምታ ጋር
የተገፋ የኩባንያው ሰራተኞች
ግልባጭ:
~ለክቡር ዶ/ር ሸህ ሙሀመድ አሊ አላሙዲ
~ለሚድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኩባንያ
~ ለኩባንያው ባለ አክሲዬኖች
~ለሁሉም የሚዲያ ድርጅቶች
~ለማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ባሉበት