banner

መጪውን የዘመን መለወጫ በአል ምክንያት በማድረግ ሁሉማርኬት ከታሜሶል ኮሚኒኬሽን እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር በ

መጪውን የዘመን መለወጫ በአል ምክንያት በማድረግ ሁሉማርኬት ከታሜሶል ኮሚኒኬሽን እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተከናወነ ባለው “ሲቢኢ ኤክስፖ 2017” በአይነቱ ለየት ያለ ሁሉማርኬት የተሰኘ መንደር መተግበሩን አሳወቀ።

የኢንፊኒቲ ቴከኖሎጂ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ልዕል መኮነን ሁሉማርኬት የተሰኘ መንደር መተግበሩን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት ከ50 በላይ ለሚሆኑ የተመረጡ አነስተኛ እና
መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ በማድረግ 150 በላይ የስራ እድልን የፈጠረ ሲሆን በገንዘብ ሲተመን ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚደርስ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት የሆኑትን የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በዲጂታል መተግበሪያ የስራ ትስስር በመፍጠር ውጤታማ ማድረግ አንደኛው አላማው አድርጎ የተመሠረተው ኢንፊኒቲ ቴከኖሎጂ በሁሉማርኬት የንግድ መንደር ከንግድ ተደራሺነት ባሻገር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን በማፋጠን ትልቅ የስራ እድልን እየፈጠረ እንደሚገኝ አቶ ልዕል መኮነን ገልጸዋል።

የሁሉማርኬት መንደር የተለያዩ ዲጂታል ነጋዴዎችን የያዘ ሲሆን የተለያዩ ልብሶች ጫማዎች፣ የቤት እቃዎችህን ፣ ዲጂታል ስልኮችን እንዲሁም እኛው ሃገር የተሰሩ የእጅ ስራ ውጤቶችን ለጎቢኚዎች ክፍት ተደርገዋል።

የኢንፈነቲ ቴክኖሎጂ በቴከኖሎጂው ዘርፍ ችግር ፈቺ የሆኑ አገር በቀል የቴከኖሎጂ ስራዎችህን፣ ሶፍትዌሮችን ለተጠቃሚዎች በማድረስ የላቀ አስተዋፅኦ አያበረከተ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሁሉግራም የተሰኘ በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የሶሻል ሚዲያ ኘላትፎርም አስተዋውቋል።

በዚህም መተግበሪያ ከ 1.5 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍርት የታቻለ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ሁሉማርኬት የተሰኘ በቀላሉ እቃ መሸጥ መግዛት የሚያስችል ዲጂታል ባዛር ለተጠቃሚዎች አቅርባል።





1 comment

Elias Getahun September 8, 2024 - 11:05 am

17 ግን የት ነሽ🤔

Reply

Leave a Comment