banner

እናት ባንክ እንቁጣጣሽን ከመሰረት በግ አድራጎት ድርጅት ህፃናት ጋር አከበረ

#FastMereja

እናት ባንክ አዲስ አመትን በመሰረት በጎ አድራጎት ድርጀት ከሚገኙ ህጻናት ጋር በዛሬው እለት ጷጉሜ 5/2016 ዓ.ም የምሳ ግብዣ እና የ150 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በጋራ አክብሯል።

የመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት የኘሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መስፍን ተገኔ እንደገለፁት እናት ባንክ መጪውን አዲስ አመት አስመልክቶ በተቋሙ ለሚገኙ እናቶች እና ህፃናት የምሳ ግብዣ እንዲሁም ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ህብረተሰቡ በአሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማስታወስ አቅመ ዳካሞችን በመደገፍ እንዲሁም በተቋሙ ለሚገኙ እናቶች የስራ እድሎችን በማመቻቸት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

እናት ባንክ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በኩል ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት በየጊዜው የተለያዩ የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ እያበረከተ ይገኛል።

ባንኩ ልዩ ልዩ ድጋፎችን ከሚሰጡ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋራ በመተባበር፣ በባንኩ ውስጥ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ማድረጉ እና በሌሎች እናቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ማኅበራዊ ኃላፊነቶች እየተወጣ እንደሆነ ተነግሯል።

📷 FastMereja





Leave a Comment