banner

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው ስምምነት “መጠናቀቀን” እና ወደ ህጋዊ ስምምነት ሊሸጋገር መሆኑን አስታወቀች

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የባህር በር የመግባቢያ ስምምነት “መጠናቀቁን” እና ወደ ህጋዊ ስምምነት ሊሸጋገር መሆኑን የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዶ/ር ኢሳ ካይድ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት በትላንትናው ዕለት በ #ሀርጌሳ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቶች በቀጠናው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ማብራሪያ ነው።

የሶማሊላንድ መንግስት በጎረቤት ሶማሊያ የ #ግብጽ ወታደራዊ ኃይሎች መስፈራቸው በእጅጉ እንደሚያሳስበውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢሳ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሚንስትሩ የሶማሊላንድ መንግስት በሀርጌሳ የሚገኘውን የግብጽ የባህል ቤተ መጽሓፍትን ለመዝጋት መወሰኑን አስታውቀዋል። በ72 ሰዓት ውስጥ ሰራተኞቹ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መሰጠቱም ተገልጿል።

የግብፅ ወታደሮች፣ መሳሪያዎችና ወታደራዊ አውሮፕላኖች በሶማሊያ ማሰማራቷ ይታወቃል። ይህ ሂደት 10 ሺህ የሚደርሱ የግብፅ ወታደሮችን በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደው አካል ነው።

ወታደሮቹ በ #ኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ማለትም በጌዶ፣ በሂራን እና በባይ ባኮል ስፍራዎች ላይ እንደሚሰፍሩ ተገልጿል።

ድርጊቱ በቀጠናው ላይ ከፈተኛ ውጥረት እያስከተለ የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ቀጠናውን ለማተራመስ የሚሰሩ ተዋናዮችን እንደማይታገስና ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል።

(አዲስ ስታንዳርድ)

7 comments

እዮብ መኮንን September 12, 2024 - 10:25 am

ጥሩ ዜና

Reply
Yeabisira YM September 12, 2024 - 10:25 am

Welcome comment section coffee or tea

Reply
Hamid Hussien September 12, 2024 - 10:26 am

Ye chereka wodeb yelem belawale alu en Somali

Reply
Biniam Junior September 12, 2024 - 10:26 am

💚

Reply
እዮብ መኮንን September 12, 2024 - 10:27 am

ኢትዮጵያን ለጦርነት ተዘጋጁ

Reply
Abdellovich Badegov September 12, 2024 - 10:29 am

እነሆ ጨቅላው ጠ/ሚ ከኢትዮጵያ አልፎ ምስራቅ አፍሪካን የማተራመስ ስራውን በይፋ ጀምሯል

Reply
Ararso Kia Hankamo Jr. September 12, 2024 - 10:31 am

ሀገሬን አትንኳት🇪🇹❣️

Reply

Leave a Comment