banner

ሰኞ ምሽት በዓለም ያሉ የአርሰናል ደጋፊዎችን በድንጋጤ ወዲያ ወዲህ ያስባለ ክስተት:: ያልታሰበው ሆነ ብዙዎች “ዓላማ ቢስ/ ት

ሰኞ ምሽት በዓለም ያሉ የአርሰናል ደጋፊዎችን በድንጋጤ ወዲያ ወዲህ ያስባለ ክስተት:: ያልታሰበው ሆነ ብዙዎች “ዓላማ ቢስ/ ትርጉም የለሽ ” በሚሉት ኢንተርናሽናል ብሬክ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ከባድ ጉዳት ተስተናገደ በአርሰናል ቡድን የልብ ምት የሆነው እና በዕለቱ ለኖርዌይ ብሔራዊ ግዳጅ የተሰለፈው ማርቲን ኦድጋርድ ላይ::

ነገሩን የበለጠ ከባድ ያደረገው እና ሚኬል አርቴታን ያስደነገጠው በአጠቃላይ ቡድኑን ያስጨነቀው አርሰና ከፊቱ ያሉት ከባድ መርሃግብሮች በሰባት ቀናት ሶስት ጨዋታዎች (ስፐርስ አታላንታ እና ማን.ሲቲ) :: ይህ ማለት አርሰናል በጉዳት እና ቅጣት ቀድሞም ባጣቸው ተጫዋቾች ላይ የማርቲን ኦድጋርድ ሲጨመር የአሰልጣኙን ዕቅድ እንደሚያከሽፍ ግልፅ ነው::

ታድያ በኖርዌያዊው ላይ የነበረው ዕቅድ እንዴት ይስተካከላል ያለእርሱ ቡድኑ እንዴት እንዲሰራ ማድረግ ይቻላል?

አማካዩ በቁርጭምጭሚቱ ያስተናገደው ጉዳት አሰቃቂ ነበር:: ሆኖም በመጀመሪያ ከጉዳቱ በሗላ ጨዋታ ማድረግ አለማድረጉ 50/50 ነበር አሁን ላይ ግን ይህ አጠራጣሪ ነው ከ3-4 ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል::

አርሰናል ሁለት የውድድር ዘመናትን የመጨረሻውን መሰናክል መዝለል ተቸግሮ በሚያሳዝን ሁኔታ ዋንጫ አጥቷል:: ይህ የውድድር ዘመን ግን “የእኛ ነው” እያሉ ላሉ የአርሰናል ደጋፊዎች አሁንም በኦድጋርድ ጉዳት ምክንያት ይሰናከል እንደሆነ ስጋት አላቸው::

የቡድኑ አጀማመር ይህ የውድድር ዘመን “የእኛ ነው” የሚለውን ስሜት የሚያጠናክር ነበር:: ስሜቱ የተዘባረቀው ቡድኑ በብራይተን ነጥብ በጣለ ጊዜ እና የተጫዋቾች ጉዳት በተደራረበ ጊዜ ነው:: ደግሞም የ105ሚ.ፓውንዱን ተጫዋች በሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ አያገኙትም በቅጣት::

ከሁሉ የባሰው ግን የኦድጋርድ ጉዳት ነው:: በሚገርም ሁኔታ ግን ክለቡ የፕ.ሊግ ኮከብ በቡድኑ ነበረው የኖርዌያዊው ትክክለኛ ተተኪ::

ዴክላን ራይስን በቅጣት ማርቲን ኦድጋርድን በጉዳት ላጣው አርሰናል ቶማስ ፓርቴ እና ጆርጊኒሆ እንደሚጣመሩ ይጠበቃል ምንም እንኳ ለኦድጋርድ ተፈጥሯዊ ተተተኪ ባይሆኑም:: አርሰናል ባለፈው የውድድር ዘመን በርቀት ለመጓዙ የአምበሉ አስተዋጽኦ አስደናቂ ነበር 22 ጎሎች እና አሲስት ይህንን ተጫዋች ማጣት ለቡድኑ ኮስታራ እክል ነው::

ኤቤሬቼ ኤዜ ለምን ተስማሚ/በጣም ጥሩ ተተኪ ይሆናል?

አዎ ከላይ ቅድም የተጠቀሰው የሊጉ ኮከብ የቀድሞው የአርሰናል ወጣት ኤቤሬቼ ኤዜ ነው:: የክለቡ ታዳጊቡድን አባል የነበረው (ከ9-13 ዓመት) “በጣም ትንሽ” በሚል ክለቡን እንዲለቅ የተደረገው::

ከዚያ እንግሊዛዊው ማረፊያውን QPR ከማድረጉ በፊት በታዳጊዎች ቡድን ውስጥ በፉልሃም እና ሌሎች ክለቦች ጊዜ አሳልፏል:: ከዚያም በሰት ወደ ሌላ ክለብ በዋና ቡድን ውስጥ ተሰላፊ ሆኖ ከዚያም በ2020 በ20ሚ.ፓ ክሪስታል ፓላስን ለመቀላቀል ክለቡን ለቀቀ:: በዚህ ሁሉ ጊዜያት ግን ተጫዋቹ አየተሞረደና ማንፀባረቅ እየጀመረ ነበር:: ከጉዳት ጋር ውየታገለም እራሱን ለማሳየት ጥረቱን ቀጥሏል:: አሁን ላይ ተጫዋቹ ከ 68-70ሚ.ፓ ዋጋ ተለጥፎበታል:: በተጠናቀቀው የዝውውር መስኮት ከፍፃሜ አልደረሰም እንጂ አርሰናል ከተጫዋቹ ጋር ስሙ ተያይዞ ነበር:: አሁን ከኦድጋርድ ጉዳት በሗላ ግን ክለቡን ምነው በዝውውሩ በገፋሁ እዚህ ዝውውር ላይ በተጋሁ የሚያሰኝ ነው:: የተጫዋቹ ሁለገብነት (versatility) አሁን ላለው አስቸጋሪ ሁኔታ መልስ ሊሆን ስለሚችል::

በእግር ኳስ ሙያው በሜዳው ሁሉም ክፍል ተጫውቷል:: በብዛት የተጫወተበት ቦታ (position) (105 ጨዋታዎች) የአጥቂ አማካይ (AM) ሆኖ ነው:: በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በብቃት አሳይቷል 11 ጎሎች 6 ለጎል አመቻችቶ ያቀበላቸው ኳሶች:: ያለጥርጥር አሁን ኦድጋርድን ላጣው ቡድን የፈጠራውን እና የማጥቃቱን ጫና ማቅለል መካፈል ይችል ነበር::

ነገር ግን አርሰናል በተጫዋቹ ላይ ውሳኔውን ያሳለፈው ከ13 ዓመታት በፊት ነበር :: ኤዜም በተሰጥኦው እየተጋ ነው ኮስታራ ሆኗል:: መቼም በሰሜን ለንደን ቆይቶ ቢሆን ምን ይፈጠር እንደነበር ማሰብ ይቻላል:: ከዚህ በተጨማሪ ግን ክለቡ አሁንም ተጫዋቹን መልሶ የማግኘት ዕድል አለው::

አሁን ታድያ የአማካይ ክፍሉ ክፍተት በማን እና እንዴት ይሞላ?

አንዱ አማራጭ ካይ ሃቫትዝን ከአጥቂ ጀርባ ሚና መስጠት ከ ፓርቴ እና ጆርጊኒሆ ጋር::

አርቴታ በካይ ሃቫትዝ ላይ የሚኖረው ሃሳብ የበለጠ የተከላካይ አማካይ መልክ እንዲኖረው ከሆነ ዩሪያን ቲምበርን ወደ መሀል ይገፋዋል:: ቲምበር እስካሁን አማካይ ቦታ ላይ የተጫወተው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው:: ወደ ክለቡ ይመጣው እንደ መሀል ተከላካይ ነው ነገር ግን እንደ inverted full-back (ወደ አማካይነት የሚገለበጥ) ሆኖ ታይቷል:: ምናልባትም የአጭር ጊዜ መፍትሔ ሊሆን ይችላል::

🎈ሰላም ጎሳዬ ለፋስት መረጃ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ




Leave a Comment