#FastMereja
ኑቢያ ስቱዲዮ ከኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ጋር በመተባበር “አቴቴ አያና ሐዎታ” የተሰኘውን ዘጋቢ ፊልም በአዲሰ አበባ መስከረም 8/2017 ዓ.ም ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ አባ ገዳዎች ታዋቂ አርቲስቶች፣ ሓዳ ሲንቄዎች በተገኙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል እንደሚመረቅ ዛሬ መስከረም 4/2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል፡፡
ይህ ዶክሜንተሪ ፊልም የገዳን ስርአትን ታላቅነት፣ የአፍሪካዊያን ኩራትና የማንንታቸው ዲሞክሲያዊ መገለጫና ከሰለጠነው አለም ባልተናነሰ መልኩ ከፍ የሚያደርገን ስርአትን፣ ሙሉነትን፣ የሰው ልጅን የተፈጥሮ መብቱን፣ ከእግዚአብሄር በታች ያሉ ፍጥረታትን የመጠበቅና የማስተዳደር ስርአት መሆኑን የሚገልጽ፣ ሰፋ ባለ መልኩ ደግሞ የሲንቄን ስርአትና የልጃገረዶች ወዮማ ስርአትን የሚያብራራና የሚገልጽ ነው ተብሏል።
ይህንን ዶክሜንተሪ ለመራስት ሁለት አመት የፈጀ ሲሆን በስራው ላይም በኦሮሞ ታሪክ ከፍተኛ፣ ልዩ ምርምርና ጥናቶችን ያደረጉ ምሁራን በጥንቃቄና በጥራት የተሳተፉበት ሲሆን ስራው አለማቀፋዊ እንዲሆን እያንዳንዷ ጥናታዊ ጽሁፍና ቀረጻ እውነትን፣ መረጃንና እውቀትን እንድትይዝ ተደርጓል፡፡ በዚህ ዶክሜንተሪ ፊልም ከምሁራን በመለስ የተሳተፉ አርቲስቶች በርካታ ሲሆኑ ታዋቂ ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡ ከተሳተፉት መካከል የተወሰኑትን ለመግለጽ ያክል አዴ ሳራ ዱቤ፣ አዴ ኑሬ፣ ሆንፋሮ፣ አዴግርጃ አኖታ፣ኦቦ ሌኒን ቁቶ፣ ዶ/ር ሙሀመድ ነሞ እና ሚስ- ሀሊማ አብዱልሼኩ የተሳተፉ ሲሆን የዶክሜንተሪውን ሙዚቃ አርቲስት ባሳ ከድር ያዘጋጀው ሲሆን ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሳም ተሳትፎበታል፡፡
በአጠቃላይ ይህንን ዶክሜታሪ ሰርቶ ለመጨረስ ከ4,000000 (አራት ሚሊዮን) ብር በላይ የጨረሰ ሲሆን አስገራሚ የሆኑ የሀገራችን አካባቢዎች፣ ለኢኮ ቱሪዝም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ቦታዎች እንደ አዲስ አበባ፣ አዳባ፣ አዶላ እንዲሁም የባሌ አካባቢን በዶክሜንተሪ ቀረጻው ለማካተት ተችሏል ተብሏል ። የዚህ ፊልም ውበቱና ጥራቱ አለማቀፋዊ ደረጃውን እንዲጠብቅ ዳይሬክቲንጉን ሮብሰን ዋቤ የተጠበበበት ሲሆን፣ በኑቢያ ፊልም ፕሮዳክሽን በኩል ለአለማችን ለእይታ ሊበቃ ችሏል ተብሏል።





6 comments
ወገን በኦሮምኛ ፃፉ እንጂ !
የጥንቆላ መንፈስ የተወጋ ይሁን😌
ህዝቅኤል ገቢሳን የሚመስሉ ታሪክ አዋቂነን ባዮች ካሉበት ሳይታይ ከስሯል
የፎለቲካ ፊልም
አሁን በሁሉም ቀበሌዎች ይከፈታል
ወደ ድንቁርና ጨለማ ጉዞ ወደ ኋላ💀😀
የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ የሚለው መፅሓፍ አንቡቡ ምስጢሩ ይገለጥላቸዋ