በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ኦርቶዶክስ፣ ወንጌል አማኞች እና ሙስሊም ሴት ታራሚዎች እንደየሃይማኖታቸው በሳምንት ሦስት ቀን የመንፈሳዊ አገልግሎት መሰጠት ተጀምሯል።
ይህም ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ፅህፈት ቤት ጋር በጋራ በመሆን እንደሚሰራ አራዳ ኤፍ ኤም ሰምቷል።
ዜጎች በተቀመጠው የሕግ አግባብ ሊቀጡ ቢችሉም ባህሪያቸውን ለማነፅና ማህበራዊ እሴቶቻቸውን እንዲያዳብሩ ለማስቻል ግን መንፈሳዊ ትምህርቶች ጉልህ ሚና እንዳላቸው፥ በማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሴቶች ማረሚያና ማረፊያ ማዕከል ዳይሬክተር ኮማንደር አይናለም ሳህሉ ለጣቢያችን ገልፀዋል።
ማረሚያ ቤቱ ታራሚዎችን ለማረም ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ እንዲሁም የስነልቦና ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ መንፈሳዊ ትምህርቶች ለእርምት ስርዓቱ ያግዙኛል ነው ያለው።
ታራሚዎች ጥፋት ሰርተው ማረሚያ ቤት ከገቡ በኋላ ፀፀትና ከፍተኛ ድባቴ ውስጥ ይገባሉ ያሉት ኮማንደር አይናለም አገልግሎቱ ከተጀመረ በኋላ ግን ታራሚዎቹ “መረጋጋትና ሰላማዊ እንቅልፍ መተኛት ጀምረናል” ማለታቸውን አስረድተዋል።
ሃይማኖታዊ ትምህርቶቹ ለጊዜው ለሴት ታራሚዎች ብቻ የሚሰጡ ቢሆንም በተያዘው 2017 ዓ.ም ግን በሁሉም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አገልግሎቱን ለመስጠት እቅድ ተይዟል ብለዋል።
ዘገባው የአራዳ ሬዲዮ ነው።

5 comments
deg…
እየሱስ ያድናል ‼️
ስሙንም ሲናስ ማረሚያ በሉት
ከዛ አንዳንድ የሀሰት ነቢያት ይገቡና “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ መግባት ስለሌለበት ይውጣልን እና ብቻችንን እናስተምር፣ በዛ ላይ የንስሀ አገልግሎት እንሰጥ….”
ከዛ ከ9 በኋላ የታራሚው ቁጥር እጥፍ ይሆናል።
ጌታ ይህን እስርቤት ሰባብራቹ ስታመልጡ ያሳየኛል🤣