0
#FastMereja
አርቲስት አደም መሐመድ የ2017 ኢሬቻን በማስመልከት የጉጂ ባህልን የሚያሳይ “ሹቢቱ” የተሰኘ ነጠላ ዘፈን ከድምፃዊት ሀሊማ አብደላ ያቀነቀኑትን ለህዝብ ጆሮ ለማድረስ ዝግጅታቸውን አጠናቀው በአርቲስት አደም መሀመድ ዩቲብ ቻናል ላይ እንደሚለቀቅ ተገልጿል።
ይህ ነጠላ ዜማ ክሊፑን ለመቅረፅና ለማሰናዳት ከ50 በላይ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት ተነግሯል።
ብርሀን ዘሪሁን በቅንብር፣ አብርሀም ኪዳኔ በማስተሪንግ እና ሚክሲንግ እንደተሳተፉበት ታውቋል። ክሊፑን ዳይሬክት በማድረግ አርቲስት ፋንታ ስንታየሁ ተጠቦበታል። Ya’a Entertainment የቪዲዮ ክሊፑን ቀረፃ አከናውናል።
አርቲስት አደም መሐመድ በቅርቡ “ኦሮሚያ” የተሰኘ የአልበም ስራ ለህዝብ ጆሮ አድርሶ ነበር፣ «Shubbittuu» እና «Obbe Dansoolee» የተሰኙ ነጠላ ዜማዎች ተወዳጅነትን ያተረፈበት ነጠላ ዜማዎች ናቸው።

1 comment
❌❌❌❌❌❌❌