0
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ኢትዮጵያ “በሶማሊያ ጎርፍ እንዲከሰት ሆን ብላ ከግድቦቿ ውሃ እየለቀቀች ነው” ሲሉ ከሰሱ።
ፕሬዝዳንቱ በሞቃዲሾ መስከረም 20፣ 2017 ዓ/ም ከዘኢኮኖሚስት ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ፤ በሶማሊያ በጎርፍ የተጥለቀለቁ አካባቢዎችን ፎቶግራፎች አቅርበው፤ ድርጊቱን ኢትዮጵያ ፈጸመዋለች ሲሉ ከሰዋል።
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ኢትዮጵያ በድንበር አቅራቢያ “በጎሳ ለተመሰረቱ ለሶማሊያ ሚሊሻዎች ትጥቅ እያስተላለፈች ነው” ሲሉ ክስ አቅርበዋል። እነዚህ መሳሪያዎች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው “በአልሸባብ እጅ ሊወድቁ ይችላሉ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
አክለውም ኢትዮጵያ “የግብፅ ወታደሮች ስምሪትን እንዲቃወሙ በሶማሊያ ውስጥ ያሉ የጎሳ መሪዎችን እና የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እያበረታታች ነው” ሲሉም ከሰዋል ሲል አዲስ ስታንዳረድ ነው ያስነበበው።

10 comments
እንኳን ለጎርፎ እሚሆን ለኢሬቻም አጥተናል😁
ኢጂጂጂጂጂጂ
😥
ልበላዋትን ያሰቡትን አሞራ ይላሉ ጅግራ
እኔም ቋንቋ ብችል እንድትበጣጠሱ ነው የምያረገው ምክንያቱም ለናንተሰላም ለመጠበቅ ሱማሊያ ምድር የወደቀ ኢትዮጵያዊ አጥንት እስከአሁን አልተመለሰምደ
ክስ ከመመስረት በፍት ለግብፅ መላላኳን ብታቆም ይሻላታል።
አልያም ይቀጥላል አንቺ ዉርደታብስ😏 መቼ አይተሽ🤨
ደግ አረገቻ
Aye alememar degu
ኢሬቻን ሞቃዲሾ ላይ ልናከብር ነዋ😜
የቆየ መረጃ ነው