0
#FastMereja l የአፍሪካ ቀንድ የሠላም Advocacy ስልታዊ እቅድ የመክፈቻ ሥነሥርአት እና ሲምፖዚየም ለሁለት ቀናት በሒልተን ሊካሄድ ነው ተብሏል።
“የምንፈልጋት አፍሪካ” (the Africa we want) የሁነቱ ርዕሰ ጉዳይ ነው።
ዝግጅቱን American Friends Community Services እና Bread for fhe World በጋራ አዘጋጅተውታል።
በዚህ ትልቅ ዝግጅት ላይ አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሲቪክ ማህበረሰብ አካላት ፣የሀይማኖት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች ፣የአፍሪካ ህብረት ፣የአውሮፓውያን ህብረት ፣የኢጋድ እና የመንግሥት አካላት ይሣተፋሉ።
ሁነቱ ጥቅምት 6 እና 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ለሁለት ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።
የዝግጅቱ መሪ ሐሳብ እስከ 2033 የሚዘልቅ ሲሆን ይህም የስድስት ዓመት ፕሮግራም ሠላምን በተመለከተ የተለየ ሀሣብን ይዞ መጥቷል ተብሎ ይታሠባል።


1 comment
መርዎቿን ወደ አረብ ሀገር በስዴት ከሄዱ ሰላም ትሆናለች