banner

አማኑኤል ሆስፒታል በቀን በአማካይ 500 ታካሚዎች በተመላላሽ ሕክምና እያገኙ መሆኑ ተገለፀ

#FastMereja l አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአዕምሮ ሕክምና በተጨማሪ ለታካሚዎች የተሟላ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ሆስፒታሉ ላለፉት 85 ዓመታት ሕብረተሰቡን ሲያገለግል መቆየቱን የገለጹት የሆስፒታሉ የሕክምና ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ኃይሌ÷ ተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ የባለሙያ ስብጥርና የሕክምና ግብዓቶችን እያሟላ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ላይም በድንገተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በ239 አልጋዎች የአስተኝቶ ሕክምናና በቀን በአማካይ 500 ታካሚዎች በተመላላሽ ሕክምና እያገኙ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የሆስፒታሉ ታካሚዎች ከአዕምሮ ሕክምና ውጭ ተጨማሪ የጤና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሌሎች የጤና ተቋማት በመሄድ ሲገለገሉ መቆየታቸውን አስታውሰው÷ አሁን ላይ ተቋሙ አድማሱን በማስፋት ለታካሚዎች የተሟላ ሕክምና ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም የባለሙያዎች ቅጥርና የሕንጻ ግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው÷ እስከ ጥር 2017 ዓ.ም ድረስ በሆስፒታሉ የተሟላ አገልግሎት ለመጀመር መታቀዱን አመላክተዋል፡፡

በቀጣይም ለአካባቢው ሕብረተሰብ የተሟላ ሕክምና የመስጠት ውጥን መያዙን ጠቅሰው÷ ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስችል ድጋፍ ማድረግ የሚችሉ አካላት ከሆስፒታሉ ጋር ተባብረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ከኢዜአ ዘገባ ተመልክተናል።

6 comments

እዮብ መኮንን October 15, 2024 - 7:48 am

አብዛኞቹ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው

Reply
PoPî Carry October 15, 2024 - 7:49 am

ፋኖ እየመጣ ነው😍

Reply
Eyobyna Boss October 15, 2024 - 7:49 am

ያሳዝናል ሀገሬ ከመሪ እስከተመሪ የለምኮ 😭

Reply
Fiker Selam October 15, 2024 - 7:49 am

ቤቱ በአብይ አህመድ የፈረስበት ሕዝብ ባያብድ ነበር የሚገርመኝ !!!

Reply
Tamirat Melese Adamu October 15, 2024 - 7:49 am

ኑሮ በዚህ ከቀጠለ ከትንሽ ግዜ በኋላ1,000,000 ሰዉ ይመላለሳል ተብሎ ይጠበቃ

Reply
Kalkidan Dawit October 15, 2024 - 7:49 am

ለዛ ነው ሰውየው ሰሞኑን ሲመላለስ የነበረው።

እኔ እኮ ለጉብኝት ነበር የመሰለኝ

Reply

Leave a Comment