0
ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአውሮፕላን አንወርድም በማለት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው የተከሰሱት ስድስት ግለሰቦች ላይ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ የተደረገባቸውን የዋስትና ጥያቄን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አፀና።
ከ15 ቀናት በፊት በስር ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።
ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ የተባሉ ተከሳሾች ግን በጠበቆቻቸው አማካኝነት የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ነበር።
ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የይግባኝ ባዮችን አቤቱታን እና የከሳሽ ዐቃቤ ሕግ መልስ፣ የግራ ቀኝ ክርክርን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ ከህግ አንጻር ተገቢ ነው በማለት ብይኑን በማጽናቱ ተከሳሾች በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ይከታተላሉ።
ዘገባው የፋና ነው።

10 comments
🔑የዋስትና መብት
የዋስትና መብት ማለት በወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ የሚያዝ ሰዉ ከእስር የሚፈታበት ስነ-ስርዓት ነዉ። ማንም ሰዉ ከህጉ ዉጪ መታሰር የለበትም የሚለዉን የህገ መንግስቱ ድንጋጌ የሚረዳ መብት ነዉ። ዋስትናም ፍርድ ቤት ከመቅረብ በፊት ወይም በኋላ ለሰጥ ይችላል። በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ አንቀጽ 28 መሰረት ጽኑ እስራት የማያስቀጣ ወንጀል፣ወንጀል ስለመፈጸሙ ጥርጣሬ ካለ እና ተጠርጣሪዉ ወንጀሉን እንደፈጸመ አጥራጣሪ ከሆነ ፍርድ ቤት መቅረብ ሳያስፈልግ ፖሊስ በዋስትና መልቀቅ እንደሚችል ይደነግጋለ። በዚሁ ህግ አንቀጽ 63 ስር ደግሞ ፍርድ ቤት ሞት ቅጣት ወይም 15 አመት እና ከዛ በላይ ጽኑ እስራት የማያስቅጣ ወንጀል ከሆነ እና ተጎጂዉ ካልሞተ ዋስትና አስፈርሞ መልቀቅ እንደሚችል ያስቀምልጣ።
ዋስትና የሚከለከልባቸዉ ሁኔታዎች
በወ/መ/ስ/ስ/ህግ መሰረት ተጠርጣሪዉ
-ግዴታዉን እንደማይወጣ ከታወቀ
– ቢለቀቅ ሌላ ወንጀል ይፈጽማል ተብሎ ሲገመት
-ማስረጃ ያጣፋል ወይም ያሸሻል ተብሎ ከታመነ
– በዚህ ህግ አንቀጽ 63 እና 28 ላይ የተገለጸዉ በተቃራኒ ተሙዋለቶ ከተገኘ
ከልዩ ህጎች ለምሳሌ የጸረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007 መሰረት
-ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ ወንጀል ከሆነ
-ከ4 አመት በላይ እና ክ10 አመት በታች የሚያስቀጡ ወንጀሎች በተደራራቢነት ተፈጽመዉ ድምራቸዉ ክ10 አመት በላይ ካስቀጣ ዋስትና አይፈቀድም።
ከዚህም በተጨማሪ በሌሎች ልዩ ህጎች በተቀመጡ ምክንያቶች ዋስትና ሊከለከል ይችላል።
ስለ ዋስትና ህግ የሚደነግጉ ህጎች
1. ህገ-መንግስት (አንቀጽ 19)
2. የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ (አንቀጽ 28፣ ከ 63-79)
3. የጸረ-ሙስና ልዩ የስነ-ስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ከማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 882/2007
4. የሰበር ዉሳኔዎች ለምሳሌ ያህል ቅጽ 19 መ/ቁጥር 112725
እና የመሳሰሉት ናቸዉ።
የዋስትና መብት በምን ሊቁዋረጥ ይችላል?
1. ክስ ሲቁዋረጥ
2. በመደበኛ ክርክር ዋስትና ሲያዝ የጊዜ ቀጠሮ
3. ከወንጀል ነጻ መባል
4. ጥፋተኝንት ዉሳኔ ተሰጥቶ ተከሳሹ ቅጣቱን እየፈጸመ ፍ/ቤቱ ዋስትና ይመለስ ሲል
5. የዋስትና ይዉረድልኝ ተብሎ ዋሱ ተከሳሹን በችሎት ሲያቀርብ
6. ዋሱ ሲሞት
7. የዋስትና ግዴታ ሳይፈጸም ሲቀር
8. በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 74 መሰረት አዲስ ማስረጃ /ጉዳይ/ሲገኝ እና የመሳሰሉት ናቸዉ።
የዋስትና መያዣ መጠን በምን ይወሰናል?
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 69 መሰረት
1. የወንጀሉ ክብደት
2. ተጠርጣሪዉ መለቀቁ ለህዝብ አስጊ ከሆነ
3. ተጠርጣሪዉ በተፈለገ ጊዜ የማይቀርብ መሆኑ
4. የተከሳሹ እና የዋሶቹ ሀብት ከግምት ይገባሉ።
የዋሶች ግዴታ
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 70፦ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ተከሳሹ ፍ/ቤት እንዲቀርብ ማድረግ።
ለዋስትና መያዣነት ምን ሊጠየቅ ይችላል?
በ/ወ/መ/ስ/ስ/ህ አንቀጽ 69 ስር የተጠቀሰዉ ከግምት ገብቶ
1.ጥሬ ብር
2. የማይንቀሳቀሱ ወይም ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች
3. የስራ ዋስ።
የአካሌ ነጻ ይዉጣልኝ ክስ የት ይቀርባል?
ፖሊስ ማንኛዉንም ተጠርጣሪ 48 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በአቅራቢያዉ ወዳለ ፍ/ቤት ማቅረብ እንዳለበት ህጉ ያስቀምጣል።…..፨ #አለ_ህግ
በለፈለፉ ይጠፉ
የመቅበጥ መጨረሻ ይሄ ነው 😪
ህጉ ለዚህ ሲሆን ይበረታል ሲያሳዝኑ
የመጀመሪያዎቹ የቲክ ቶክ ሰለባዎችና መሬት ያልረገጠ በአዬር ላይ ዝና ተንሳፋፊ ፊኛዎች!
A momentum mistake and lack of emotional intelligence can cost your life. Always have patience and don’t show off!!
ከጉርሻ ቀጥታ ነው እንዴ ኮፒ ምታደርጉት😁
ፎሎወር ከንቱ ነው ለካ።
This ain’t funny anymore! 😰
ህጉ ግን ለነዚህ ሲሆን ይበረታል ሲያሳዝኑ