#FastMereja አንጋፋ ተዋንያን እና ባለሙያዎችን የተሳተፉበት ‘የራስ መንገድ ‘ ፊልም በቴሌቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ መታየት ይጀመራል።
ሰለሞን ቦጋላ ‘የራስ መንግድ’ ፊልም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በድርሰት እና በአዘጋጅነት የተሳተፈ ሲሆን በሳቢሳ ፊልምስ ተሰርቶ ፤ በዳይሬክተር ኦፍ ፎቶግራፊ ደግሞ ዕዉቁ ባለሙያ ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) ተሳትፏበታል።
በpan african film festival ላይ ከ150 በላይ ሃገራት ከተወጣጡ ፊልሞች መካከል’የራስ መንገድ’ ፊልም ምርጥ 25 ዉስጥ በመግባት የምስክር ወረቀት ማግኘት ችሏል። ይህ ፊልም ዘመኑ የደረሰበትን የፕሮዳክሽን መሳሪያዎች በመጠቀም በከፍተኛ በጀት የተሰራ መሆኑንም የፊልሙ አዘጋጆች ገልጸዋል።
በዚህ ፊልም ላይ የሃገራችንን ዕውቅ ተዋንያኖች ሰለሞን ቦጋላ ፣ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ) ፣ ፍጹም ጸጋዬ ፣ሮማን በፍቃዱ እና ሌሎችም አንጋፋ የፊልም ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።
ቴሌቲቪ ለመዝናኛ ኢንደስትሪው በተለይም ደግሞ ለፊልም ኢንደስትሪው ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል ፤ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው አዳዲስ ፊልሞችን ብቻ ሳይሆን ለአጭር ጊዜ ታይተው ከሲኒማ የወርዱ እና ብዙ የተደከመባቸው ፊልሞችን እንደገና ለህዝብ እንዲቀርቡ ቴሌቲቪ ሁነኛ አማራጭ ሆኖ መገኘቱን የኤግልላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በእርሱፊቃድ ጌታቸው ገልጸዋል።
ቴሌቲቪ ከ”6 ሰአት ከለሊቱ” እና ‘ትዝታ’ ፊልሞች በመቀጠል ‘ዶቃ’ እና ‘ጥቁር አደይ’ የተሰኙ የተመረጡ ፊልሞችን በተከታታይ ወደ ፕላትፎርሙ ማስገባቱ ይታወቃል።
በቅርብ ጊዜ ደግሞ ብዙ ሽልማት በማግኘት እና ከተመልካችም ዘንድ ትልቅ ተወዳጅንነት ያገኘዉን ‘ቁራኛዬ’ ፊልም ቴሌቲቪን ተቀላቅሏል። ከቀናት በኋላ ደግሞ history film ያቀረበው የአለባቸው አራጌ ‘ከርቤ’ ፊልም ቴሌቲቪ መተግበሪያ ላይ እንደሚለቀቅ ማወቅ ተችሏል።
ኤግልላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ በ በርሱፊቃድ ጌታቸው የተመሰረተ የፊንቴክ ድርጅት ሲሆን በስሩ ያበለጸጋቸው ካሽጎ ፣ጉዞጎ ፣ኢትዮዳይሬክት ፣ነዳጅ ፣ዱቤአለ እና ኢት ኢዝ ማይ ዳም ተጠቃሽ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ናቸው።





1 comment
🥰