banner

ይድረስ ለድምፃዊት ሀና ግርማ

በተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

ፍቅር ፣ ፍርሀት ፣ ቃል-ኪዳን ፣ ጊዜን የሚናገር ሙዚቃ…

ቀን በጠነከረ ቁጥር የሚደመጥ ሙዚቃ ሙዚቃው ከወጣ ጀምሮ ደጋግሜ ሙዚቃውን ሰማሁት አልሰለቸኝም ሁል ጊዜ ከምሰማቸው ሙዚቃዎች ተርታ አስቀምጬዋለሁ የሐሳቡ ክብደት በእውነተኛው ዓለም አንዱ ክፍል የሆነው የግጥምና ዜማ ውህድ ቅንብር ጋር ጥምረቱን በጣም ደስ ብሎኛል ሰማሁ… ግን ነጥቦችን ላንሳ፡፡

“አልሆን ብዬ ብፈራም እንደ ሴትነቴ
ምን ቢያሳስበኝም የነገው ሕይወቴ”…

ምን መሰለህ? በታሪክ ነገራ የተዋዛ ፣ ታሪክ በብዙ መልክ ሲዳሰስ አንድም የወደፊቱን አንድም የተፈጠረውን እንደ ትውስታ በትዝታ መልክ ይወሳል፡፡ይህ ሙዚቃ ገና ሊፈጠር ያለን አስደንጋጭ ታሪክ ሆኖ እድሜን ፣ ጊዜን ፣ እምነትን ያወሳል፡፡መጀመርያ ላይ ያለውን የፍቅር ማዕበል እንዳይንደው በፍርሀት እና በጊዜ ታጥሮ ሲገለፅ ያሳያል፡፡

“እንደ ልቤ አልሆንኩ እድሜም ይሄዳል እንደ ዋዛ …
መልክም ይረግፋል እንደ ጤዛ…
እንደ ምትወደኝ ውስጤ ቢያምንም
በወረት ባጣህ ሰው አልሆንም”…

የነገ ሕይወት የተደላደለ ለማድረግ እርግጠኝነትን ይፈልጋል ነገሮች በነጎዱ ጊዜ ትኩሱ አቅም እና ጉልበት ይረግፋል በትናትናው ሚዛን ዛሬ መመዘን አይቻልም… ስለዚህ ልብም አርፎ እምነትም ፀንቶ ፍቅርን በጉልህ ማሳየት ያስፈጋል፡፡ግን በእርግጠኝነት የተሰጠን ልብን ማሸማቀቅ ብዙ የሕይወት ምስቅልቅል ውስጥ ይከታል ይህ በጣም ያስፈራል የነገ ሕይወት መግፋት ማለም ያቅራል ያስፈራል ይንን ይገልፃል፡፡

“እንደ ልቤ አልሆንኩ ቆሜ አያሳየኝ ቀን ሊከዳኝ …
ውዴ አደራህን ስለ ኪዳን”

በማንኛውም የሕይወት ሽሽግር ውስጥ “ቃልኪዳን” እጅጉኑ ጠንካራ እና እጅጉ አስፈሪ መሀላ ነው፡፡ የለት ለት ጉዞ ውስጥ እምነትን የሚፈታተን አንድም የሚያቀናህ ታላቅ ዓለት ነው፡፡ በምን መለሰህ ውስጥ ስለ ኪዳን ያወሳል እሱን ካልጠበቅን ለመጠገን ጊዜ ብቻ ሳይሆን የተጎዳ ሞራል ማከም ጥሞና መውሰድ በጣም ጊዜ ይወዳል፡፡ ይህ ሙዚቃ ይንን ይናገራል፡፡ በምን መሰለህ? እንዳልጎዳ ጠብቀኝ …የፍቅርህ ቃላቶች እና ድርጊቶችን እውነትነታቸው እስከ እድሜ እርጅናችን ይቀጥል አትጉዳኝ እባክህ ስትል በፍቅር ጭንቀት ትገልፃለች፡፡

ምን መሰለህ ?…ያስጨንቀኛል
ምን መሰለህ? ገና ለገና
ምን መሰለህ? ባጣህስ ብዬ ሴት ልጅ እና

ፍርሀትን በፍቅር ውስጥ ሲንፀባረቅ ያሳያል “ሴትልጅ ነኝ” የሚለው ቃው ብዙ ትርጓሜ ይሰጠዋል አንደኛው እድሜ ነው እድሜ ሲነጉድ ብዙ ነገርን ያሳጣል ሁለተኛው ሕይወትን የነገው ህልም ያስጨንቃል፡፡ ይንን በማሰብ “ያ” የመለያየት አስከፊው በሽታ እንዳይወጣ ፍርሀቷን ትናገራለች፡፡

ለምኔ ለምኔ
ሌላ አያለሁ በዓይኔ…

ይንን ሙዚቃ የከወኑት ከያኒያኖች በግጥም ዜማ አብዲ… የአብዲ የግጥም ምሽጎቹ ልክ እንደ ስሜታቸው ከጥዑም ዜማዎች ጋር በአንዴ ውህድ ይፈጥራሉ ይንን መታደል ይመስለኛል፡፡ ታምሩ አማረ የታምሩ ከለር ከምላቸው ስራዎች ናቸው፡፡ የሙዚቃ ስልት እንደ አመጣጣቸው ይገልፃቸዋል (ትዝታ ማይር ) ያለ ድንቅ ሙዚቃ፡፡ ሀና ግርማ ሕይወት የዘራችበት ሙዚቃ ነው፡፡ በዚህ ላይ የተሳተፋችሁ ቤዝ ጊታር ልዋም መሀሪ ዳሬክተር ዮሴፍ ባዬ ሁሉ እናመሰግናለን፡፡

Leave a Comment