banner

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት ምስረታ በዐሉን አከበረ!

#FastMereja I ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አስርት አመታት ያስመዘገባቸውን ታላላቅ ስኬቶች በመዘከር የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት ሲያከብር ቆይቷል፡፡

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ፌዴሬሽን ብሄራዊ አባል የሆነ በህጻናት ደህንነት ጥበቃና ልማት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ከማናቸውም ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ እሳቤዎች ገለልተኛ የሆነ አለም አቀፍ የልማት ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ከተመሰረተበት እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት፣ ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ ላይ አዎንታዊ ለውጦችን በማምጣት ላይ የሚገኝ የልማት አጋር ድርጅት ነው።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከፍ ያለ ደረጃ ያላቸው ሁነቶችን ጨምሮ የጋዜጣዊ መግለጫ፣ የፓናል ውይይት፣ የኢትዮጲያን ብሄራዊ የህፃናት ጥበቃ ስርዓትን ለማጠናከር ሊወሰዱ የሚገቡ ትግባራት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ፣ ተከታታይ የራድዮ ፕሮግራም ስርጭት፣ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እንዲሁም የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን ሲከናወኑ መቆየታቸው ተነግሯል።

የበአሉ አከባበር የተጀመረው በኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳይሬክተር አቶ ሳህለማርያም አበበ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲሆን በመቀጠልም የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ ክልል ምክትል ዳይሬክተር አቶ በድሉ ሸገን የአለም አቀፉን ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ፌዴሬሽን ፕሬዚደንትን እንዲሁም የራሳቸውን መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በንግግራቸውም ድርጅቱን “ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በተደራሽ ቁጥርም ሆነ በፕሮግራም አፈፃፀም የተዋጣለት ስራ በመስራት በምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ ክልል ውስጥ ካሉት የኤስ ኦ ኤስ ፕሮግራሞች መካከል የመሪነቱን ስፍራ ይዞ የዘለቀ ጠንካራ ድርጅት ሲሉ ገለጸውታል።

የኤስ ኦ ኤስ ስዊዘርላንድ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክቡር Mr. Alex de Gues በበኩላቸው ድርጅታቸው ከዚህ ቢፊት የገንዘብ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ እንዳበረከተ አስታውሰው ይህም ትብብርና ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በተጨማሪም የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በ50 አመታት የበጎ ተጽእኖ ጉዞው 8.1 ሚሊዮን ሰዎችን መድረስ እንደቻለ Global Exceptional Excellence Consultancy የተባለው ድርጅት ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን አመልከቷል።





1 comment

እዮብ መኮንን October 22, 2024 - 9:50 am

የኢትዮጵያ ህዝብ ያቃቸዋል

Reply

Leave a Comment