banner

የጥላቻ ንግግሮችን በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጨው 1 አመት ከ6 ወር እስራት ተቀጣ።

#FastMereja I በምዕራብ ኦሞ ዞን በባቹማ ከተማ በሀሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች በማህበራዊ ሚዲያ በፌክ አካውንት ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በ1አመት ከ6ወር ቀላል እስራት መቀጣቱ የባቹማ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ህግ ዩኒት አስታወቀ።

ተከሳሽ አቶ አቤል ታደመ ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2016 ዓ/ም ድረስ በምዕራብ ኦሞ ዞን ውስጥ ኪቺ ኪኖት የተባለ ሐሰተኛ የፌስቡክ ድረ ገጽ በመክፈት በተለያዩ ጊዜያት ሀሰተኛ መረጃዎችን እና የተለያዩ የጥላቻ ንግግሮችን በጽሑፍና በምስል በማድረግ ለህዝብ ሲያሰራጭ መቆየቱን ተገልጿል።

የባቹማ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ እና ዐቃቤ ህግ ዩኒት በጋራ በመሆን የምርመራ መዝገብ በማጣራት በቀን 24/10/2016 ዓ/ም የባቹማ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ህግ ለባቹማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 00457 የክስ ቻርጅ በሁለት ክሶች ተከሳሽ ላይ የወንጀል ክስ ማቅረቡን አስገንዝበዋል።

ተከሳሽ በመጀመሪያው ክስ የጥላቻ ንግግርን እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7(1) በመተላለፍ የቀረበ ክስ ሲሆን ክስ ሁለት በተመሳሳይ አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 5 አና 7(3) ለይ የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፎ በመገኘት የሚል መሆኑ ተጠቅሟል።

ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን ተቀብሎ ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ ክሱን እንዲከላከል መብት ቢሰጠውም ተከሳሽ ባቀረባቸው መከላከያ ማስረጃዎች ክሱን መከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ዛሬ በቀን 14/2/2017 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት በተከሳሽ አቤል ታደመ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በአንድ አመት ከስድስት ወር ቀላል እስራት እንዲ ቀጣ ፍርድ ቤቱ ወሳኔ አስተላልፏል ሲል የባቹማ ከተማ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

4 comments

ማህደር የሽወንድ October 24, 2024 - 12:36 pm

በፓርላማ የሚያሰራጭ ከሆነስ🙄

Reply
እዮብ መኮንን October 24, 2024 - 12:37 pm

የፍቅር ንግግርንስ ያሰራጨ !?

Reply
Jemila Umer October 24, 2024 - 12:39 pm

ምዕራብ ኦሞ ዞን የሚባል ከኢትዮዽያ ዉጪ አለ ወይስ የእኛ ሀገሩ ነዉ?ማን ሊተርፍ🧐

Reply
የመከራዋ ምድር ምድር ማን ነች October 24, 2024 - 12:47 pm

አሁንም ይጣራ 80% ፅንፈኛ ነው 👏👏

Reply

Leave a Comment