banner

ካንትሪ ትሬዲንግ 2ኛውን የሚሊኒየም ከቀረጥ ነፃ የመጠጥ መደብር በስካይ ላይት ሆቴል ከፈተ።

#FastMereja I ካንትሪ ትሬዲንግ ከቦሌ አየር መንገድ ቀጥሎ ሁለተኛውን ከቀረጥ ነጻ የሆነ ምርቶችን የሚሸጡበት የንግድ ማዕከል በስካይ ላይት ሆቴል ከፈተ።

በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ላለፉት አመታት ከቀረጥ ነፃ የሆኑ ምርቶችን ለተለያዩ የውጭ ሀገር ማኀበረሰብ ሲያቀርብ የነበረው ሚሊኒየም የተሰኘው ከቀረጥ ነፃ ምርቶች መሸጫ በዛሬው እለት የቀድሞ የኢትዮጵያ ኘሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ አለም አቀፍ ማኀበረሰብ አባላት በተገኙበት ቦሌ በሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል ሁለተኛው ከቀረጥ ነፃ የንግድ ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

ካንትሪ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ሚሊኒየም ከቀረጥ ነፃ የመጠጥ መደብር ላለፉት 17 ዓመታት በቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ለበርካታ ዓለም አቀፍ መንገደኞች ጥራት ያላቸዉ ምርቶች በማቅረብ የሚታወቅ ተቋሙ በቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ብቻ ተገድቦ ይሰጥ የነበረዉ የዱቲ ፍሪ አገልግሎት በአዲስ መልክ በስካይ ላይት ሆቴል ዉስጥ ለአለም አቀፍ እንግዶች፤ ለዲፕሎማቶች፣ ቱሪስቶች ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲያገለግል ተደርጎ መከፈቱ ተነግሯል።





4 comments

አልቃሽና ዘፋኝ October 24, 2024 - 8:11 pm

ዉስኪ በስም ነዉ የማዉቀዉ ምን ምን ይላል ?

Reply
Brook Alemayehu October 24, 2024 - 8:25 pm

ሰው ድህና ነገር ከቀረጥ ነፃ ብሎ ለሕዝብ ያስተዋወቃል እዝህ ዉስኪ ያስተዋዉቃል የተረገመች ሀገር

Reply
Evan Dawit Jordans October 24, 2024 - 8:26 pm

እሄ ህዝብ ምግብ ነው ምያስፈልገው urgently 😂 not 🍷

Reply
Um Amita October 24, 2024 - 8:28 pm

አተኙም እንዴ እናንተ ግን ?😕

Reply

Leave a Comment