#FastMereja I ቪታ ፉድ ኢንዱስትሪ እያመረተ ለገበያ በማቅረብ ላይ የሚገኙት ታይ ታይ ከረሜላዎች እና ሎሊ ፖፕ ምርቶቹ ሕጋዊ ምርቶች መሆናቸውን አሳወቀ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ገበያ ተመሳሳይ ምርቶች ታይተዋል ያሉት የድርጅቱ ኦፕሬሽናልና ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ኢዮኤል ጥበቡ ምርቶቹ የሚመረቱበት ቦታ ካለመታወቁ ባሻገር የሚጠቀሙት ግብዓት ምንነት ያልተረጋገጠ በመሆኑ ከጤና አንጻር የአደጋ ስጋት ከመሆናቸው ባሻገር በሕጋዊ ኢንቨስተሮች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል ብሏል።
ለመንግስት ለሚመለከታቸው አካላት አሳወቀናል ያሉት አቶ ኢዮኤል ቪታ ፉድ ኢንዱስትሪ ለምርቶቹ ተጠቃሚዎች የንግድ መደብር ባለቤቶች እና ወላጆች ቪታ ፉድ ኢንዱስትሪ ምርት የሆነው ታይ ታይ ከረሜላ ብቻ ዋናውና የተመሰከረለት ምርቱ መሆኑን ማረጋገጥ ያሻል ብሏል።
መቀመጫውን ቱርክ ያደረገውና በኢትዮጵያ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2018 ምርት የጀመረው ኪታ ፉድ ኢንዱስትሪ
ታይ ታይ የተሰኘው ከረሜላ የዓለምአቀፍ ደረጃን በመጠበቀ በማምረት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሕጻናትም ሆነ ለአዋቂዎች በሚሆን መልኩ እያቀረበ የሚገኝና ተወዳጅነትን ያገኘ ሲሆን ሌላኛው ሎሊፖፕ የተሰኘው ታዋቂ ምርቱም በማንኛውም ዕድሜ ላይ ለሚገኙ ሁሉ እንዲስማማ ተደርጎ አስተማማኝ ደስታን በሚሰጥ ጣዕም የተዘጋጀ ምርቱ እንደሆነ ነው የተገለፀው።




