banner

ደመመዝ እንዲከፈላቸው ፊርማ ያሰባሰቡ የዎላይታ ዞን መምህራን ለእስር ተዳረጉ

#FastMereja I በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ደመወዝ እንዲከፈላቸው ፊርማ በማሰባሰብ ላይ የነበሩ መምህራን ለእስር መዳረጋቸውን የታሳሪ ቤተሰቦች ገለፁ።

እስሩ የተፈጸመው መምህራኑ ከደመወዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት መሆኑን ዶቼ ቬለ ዘግቧል።

ፖሊስ መምህራኑ “አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል” እንዲሁም “የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል” በሚል ማሰሩን የታሳሪ ቤተሰቦች ገልፀዋል።

“ፖሊሶች ወደ ቤት ሲመጡ ምንም አይነት የፍርድ ቤት መያዣ ወረቀት አላሳዩም” ያሉት የመምህራኑ ቤተሰቦች አክለውም መምህራኑ ደሞዝ ይሰጠን ብለው የዳቦ ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ታሰረውብናል ሲሉ ገልጸዋል።

እንዲሁም አንድ የዳሞት ወይዴ ወረዳ መምህር በበኩላቸው የፊርማ ማሰባሰብ ስራውን ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል ሶስት በቅርብ የሚያውቋቸው መምህራን ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸው፤ ከመታሰራቸው በፊት “እረፉ” የሚል ማስጠንቀቂያ ከወረዳው ባለሥልጣናት ተሰጥቷቸው እንደነበረ ገልጸዋል።

የዎላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር ዎህዴግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጎበዜ ጎኣ በበኩላቸው መምህራኑ ያነሱት የደመወዝ ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው፤ “ደመወዝ የጠየቀን አመፅ ቀስቀሰሃል ብሎ ማሰር ከሥነምግባር ውጭ የሆነ ድርጊት ነው።” ሲሉ መግለጻቸውን ዶቼ ቬለ በዘገባው አመልክቷል።

10 comments

Frita Alex October 26, 2024 - 9:20 am

ለቤት ክራይ እና ለቀለብ ስላልበቃ አደል ደሞዛቸው ጭማሪ የጠየቁት😃
ይኸው ቤቱም ምግቡም ከመንግስት በነፃ👐
ይሄኔ የፈረሙት እኛንም በወሰዱን እያሉ ነው😉😄

Reply
የመከራዋ ምድር ምድር ማን ነች October 26, 2024 - 9:21 am

ሰርቶ ከመብላት ታስሮ መብላ ሳይሻል አይቀርም 🤔

Reply
አብርሃም ኑናቶ October 26, 2024 - 9:22 am

Nigusu Tesema
Jovani Gebeyehu

አያችሁ!?🙁🙁🙁

Reply
Zo Laä October 26, 2024 - 9:24 am

የምር የዚህ ሀገር መፍትሄው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ

ምንም አይነት መንግስት አያስፈልገንም….እኛው ህዝቦቿ እየተጨቃጨቅንም ቢሆን ብንኖር ከዚህ የተሻለ ነገር እናደርጋለን 😏

Reply
Kib Keb October 26, 2024 - 9:24 am

27 አመታት ጨለማ ነበር ?

Reply
ፍቅር ፍቅር October 26, 2024 - 9:25 am

አረ ወያኔ ማረን 🙏🙏🙏

Reply
ተስፍሾ የሚካኤል ልጅ October 26, 2024 - 9:26 am

በብልጽግና
ብዙ እናያለን ገና

ሳልፈልግ ነው የገጠመብኝ

Reply
Esmael Abbaa Jabal October 26, 2024 - 9:30 am

ሳይሰሩ ሊበሉ ነዋ 😁

Reply
Eyu Gual Sirba Abay October 26, 2024 - 9:35 am

በዚህ ወቅት መብትህን የምታስከብረው በሀይል ብቻና ብቻ ነው።

Reply
Bereket Elsae Zerfu October 26, 2024 - 9:36 am

እውነትም ብልፅግና ነው 👐👐

Reply

Leave a Comment