banner

በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ አሽከርካሪዎች እና ተራ አስከባሪዎች በስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና ሊሰጥ ነ

በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ አሽከርካሪዎች እና ተራ አስከባሪዎች በስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

#FastMereja I በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ 1ሺ 5 መቶ ለሚሆኑ አሽከርካሪዎች እና በተራ ማስከበር ስራ ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች በስነ-ምግባር ዙሪያ በመጪው ቅዳሜና እሁድ ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

ስልጠናው በሁሉም ክፍለከተሞች የሚሰጥ ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እና ህብረተሰቡን በቀናነት ለማገልግል የሚያስችል እንደሆነ ታምኗል።

ስልጠናው በቢሮው የስነምግባር እና የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት መሪነት ጥቅምት 23 እና 24 በተመረጡ ቦታዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ለአሽከርካሪዎችና በተራ ማስከበር ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ ቀርቧል፡፡

10 comments

ጆን ሳንጃው October 31, 2024 - 4:33 pm

የቲኳንዶ ስልጠና ሰጥታቹ ደሞ ተሳፋሪን እንዳታስደበድቡን😢👍

Reply
Seyfu Wodajie October 31, 2024 - 4:34 pm

ለሰለጠኑት እውቅና ና ኮድ ስጧቸው ህገ ወጡ እንዲለይ!!

Reply
Abay Filmon October 31, 2024 - 4:35 pm

በተለይ በተለይ ለወያሎች ይቅርታ ለረዳቶች ካለባበስ ጀምሮ ውይ ተቃጠልን

Reply
TaRe Chris October 31, 2024 - 4:35 pm

ስልጠናውን ትተው ሂሳቡን ይቀንሱልን

Reply
Mame Der October 31, 2024 - 4:35 pm

ስልጠና ሳይሆን ቁንጠጣ ነው የሚያስፈልጋቸው ምንም አይነት ስርዓት የለቸውም

Reply
Shewa Buna Ke Kebena October 31, 2024 - 4:36 pm

በፈጣሪ ሥም ለእኔ ከኮሪደር ልማቱ በፊት ትኩረት ሊሠጠው የሚገባ ትልቅ ሥራ ህዝብ እንባ ሣይሆን ደም እያለቀሠ መሆኑን በቶሎ ሊረዳ ይገባል

Reply
Fethi Ibnu Beydi October 31, 2024 - 4:36 pm

አፉ ላይ ተርዚና ወጥሮ ሚያናግረኝ ረዳት ሳይ ተማታ ተማታ እንደሚለኝ በዛው ሀሳብ ብትሰጡልኝ 🙏

Reply
Kibru Doge October 31, 2024 - 4:37 pm

የጉቦ አቀባበል በDigital መንገድ
ለማድረግ ይሆናል🤭

Reply
Semir Man October 31, 2024 - 4:37 pm

ስልጠናው ወታደራዊ ነው ?

Reply
Kinfe Yegebireal Liji October 31, 2024 - 4:38 pm

በነካ እጃችሁ ለጫኝና አውራጆችም አሰልጥኑልን

Reply

Leave a Comment