0
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የአሰሪ እና ሰራተኛ መምሪያ ሃላፊ የሆኑት አቶ ታሪኩ ጥላሁን እንደገለፁት በሀዋሳ ከተማ የተጀመረው የኮሊደር ልማት ግንባታዎች እንደ መንግስት ለወጣቱ የስራ ዕድል ፈጠራ ተብሎ ከተቀመጠው አቅጣጫ በተጨማሪ እንደ ትልቅ ዕድል ሆኖ ለበርካታ የከተማችንን ነዋሪዎች የስራ እድል እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።
ለሴቶች እና ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን በማፋጠን ረገድ የኮሊደር ልማቱ እያሳረፈ ያለው አሻራ ትልቅም ነው ሲሉ አቶ ታሪኩ ገልፀዋል፡፡
በከተማዋ ያልተነካ መጠነ ሰፊ የስራ ዕድል አማራጮች መኖራቸውን የጠቀሱት ሃላፊው ስራን እና ስራ ፈላጊ ዜጎችን በማቀራረብ በኩል ብዙ ስራዎች እንደ ሀዋሳ ከተማ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አሳውቀዋል፡፡
አቶ ታሪኩ አክለውም የኮሊደር ልማቱ የስራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ለወጣቱ የሞያ ግብዓት በመሆን መሰረታዊነቱን ከማረጋገጥ ባለፈ በከተማችንን እየተሰሩ ያሉ የኮሊደር ልማቶች ለወጣቶች የስራ እድል የፈጠሩ ብቻ ሳይሆኑ ከተማችንን እና የህዝባችንን ብልጽግና ያረጋገጡም ሆነዋልም ብለዋል።





7 comments
ወሬ
ባለ ግዜዉ ከተማሞችን እያስዋበ ነዉ ነገ ይጠየቅበታል 🤗
የስራ እድሉ አልደረሰኝም🙌
Ke betachw iyafenakelu sira tilalachu inde
የስራ እድል ?
ጊዜያዊ የስራ እድል
ኮሪደር ነው ወይስ ኮለደር ነዉ ፋስቶች?editorial bord የላችሁም ?
በሚገባ በሃዋሳ ከተማ እየተሰራ ያለው ነገር ተስፋ ሰጪ ነው።