
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ልዩ በረከት ያለበት ስፍራ ነው፡፡
ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያን ከመፈወስ አልፎ ሙት ያስነሳ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ከዘጠና በላይ ገዳማውያን የተጠለሉበት፣ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡
ይሁንና መነኮሳቱና ገዳማውያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነው፡፡ አከባቢው ተፈጥሮ ፊቷን አዙራበት ድርቅ በመኖሩ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆኋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው ያለው ጦርነት በየጊዜው ይጎበኟቸው የነበሩ ፀበልተኞች ፈጽመው እንዲሸሹና ገዳማውያኑ ያለምንም ጠያቂ በትልቅ ችግርና ፈተና ውስጥ እንዲገኙ አድርጓቸዋል፡፡
ከፀሎትና ከድካም መልስ የሚጠለሉበት በአታቸውን ማጽናት የሚችል እገዛ፣ ከፆም መልስ የሚቀምሱትን አፍ መሻሪያና የአመት ልብስ ልናቀርብላቸው ይገባል። በዚህ የበረከት ስራ ገዳሙንና አባቶችን ብቻ ሳይሆን በጸሎታቸው ሀገራችንንም ለመጠበቅ አስተዋጽኦ እናደርጋለን፡፡ የእያንዳንዳችን ጠብታ ድጋፍ ሲጠራቀም ዋጋ አለው፣ የሕሊና እርካታም እናገኛለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
1 comment
በዚያ ገዳም ተአምራትን የሚሠራ አምላክ እንዴት ገዳሙን ከልሙና መታደግ አቃተው?
አምላክ የሚለምኑት እንጂ የሚለምኑለት አይደለም። መነኮሳቱም ዓለምን ንቀን ገዳም ገባን ካሉ እንዴት መልሰው ዓለምን ይለምናሉ?