banner

ህይወቱ ካለፈ ሰው አካውንት ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ ለማውጣት የሞከሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በወላይታ ሶዶ በሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ እና ህይወቱ ያለፈ ሰውን ማስረጃ በመጠቀም ከባንክ ገንዘብ ለማውጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከአማራ ክልል በተፃፈ ደብዳቤ የመከላከያ አባላት መሆናቸውን የሚገልፅ እና የሟች ልጆች እንደሆኑ የሚገልጽ የውክልና ማስረጃ ለባንኩ በማቅረብ በሟች ስም የተቀመጠ 16ሚሊየን 400ሺ ብር ለማዛወር የሚያስችላቸውን ሙሉ ሒደት እየጨረሱ በነበረበት ወቅት የባንኩ ስራ አስኪያጅ ለመጨረሻ ጊዜ የውክልና ሰነዶችን ሲመረምር በመጠራጠሩ ለህግ አካል መረጃ በመስጠት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በባንኩ የተቀመጠውን ብር በስማቸው አውጥተው እንዲካፈሉ ያመቻቸ ነው የተባለ በከተማው ፋና ወንባ ቀበሌ ነዋሪ ና ቀደም ሲል የቀበሌው ጸጥታ ሀላፊ የነበረ አስራት ኤርገና የተባለ ግለሰብም በተጠርጣሪዎቹ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

ፖሊስ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩትን ሦስቱን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

Via: ዳጉ ጆርናል

10 comments

Tiku Aragie Gonete November 7, 2024 - 9:02 am

ማናጀሩ ሳይስማማ ሊደረግ አይችልም

Reply
Henok Getachew November 7, 2024 - 9:07 am

ሟቿ እራሱ ይህን ብር ከየት ነዉ ያመጣዉ ሟቿ ላይ ምርመራ ይደረግ

Reply
ስንታየው አጥላባቸው አንለይ November 7, 2024 - 9:11 am

ከአስከሬን ለይ ቀለበት የሚሰርቅ ባለበት ሀገር ለይ ይሄ ፅድቅ ነው‼

Reply
Degineh Tefo November 7, 2024 - 9:12 am

16 ሚሊዮን ያለው ሰዉ ሲሞት መንግስት ለምን ዝምታ መረጡ 😎😜

Reply
Wubetu century metal works November 7, 2024 - 9:13 am

ዱኒያ ጠፊ ናት ምንችግር አለው ቢጠቀሙ

Reply
Hagos Gidey November 7, 2024 - 9:16 am

በመኪና ኣደጋ የሞተ ሰው የኣስክሬን ምርመራ ውጤት ለመፃፍ የሻይ እሚጠይቅ ዶክተር ያላት ሀገር ኮ ናት

Reply
Fikadu Lema November 7, 2024 - 9:18 am

Min chgr alewu kemotech mewusedi newa

Reply
Endris Fentaw November 7, 2024 - 9:22 am

ሟችን ማን ገደለው..??

Reply
Teddy Tarekegn November 7, 2024 - 9:29 am

16 ሚሊዮን እያለው ለምን ሞተ እሱን አጣሩ😭😔

Reply
Shambel Melaku November 7, 2024 - 9:35 am

እሺ እነርሱ ተፍ ተፍ ብለው ሊያወጡት ባይሞክሩ ገንዘቡን ማን ሊያወጣው ነው !?

Reply

Leave a Comment