banner

ይህ አሳዛኝ መልዕክት የአንድ ኢትዮጵያዊ ጊዜያዊ ችግር ነው የሚያደርገው ሲያጣ በውስጥ መስመር መልዕክቱን እንደላከን የገለፀው፣

ይህ አሳዛኝ መልዕክት የአንድ ኢትዮጵያዊ ጊዜያዊ ችግር ነው የሚያደርገው ሲያጣ በውስጥ መስመር መልዕክቱን እንደላከን የገለፀው፣ ሁላችሁም የምትችሉትን እንድትደግፉት በፋስት መረጃ ቤተሰብ ስም እንጠይቃለን።

***

ሠላም ፋስት መረጃ እንደምን አለህ? እኔ ፍፁም እባላለሁ የምኖረው አዲስአበባ ነው። የሁለት ወንድ ልጆች አባት ነኝ ። ልጆቼ 7 እና 4 አመት ናቸው ። ወንድሜ ይሄን የፃፍኩልህ እዚሁ ፌስቡክ ላይ ከዚህ ቀደም ብዙ ግዜ እርዳታዎችን ስታደርግ የተቸገሩትን ስትደግፍ ስትረዳ ስላየሁ ነው እንደው ራሴን በዝምታ አፍኜ በጭንቀት ከምገል ተናግሬው ቢቀለኝ ብዬ የፃፍኩልህ። እባክህ እንደደፈርኩህ አድርገህ እንዳትወስድብኝ።

እኔ መሃንዲስ ነኝ ፕሮጀክት እመራ ነበር። ከዚህ ቀደም እጅግ ባይባልም መካከለኛ ጥሩ ገቢ ነበረኝ በቻልኩት ከራሴ በላይ ቤተሰቤንም አግዝ ነበረ ። አሁን ግን እጅግ የከፋ ተስፋ አስቆራጭ ችግር ውስጥ ነኝ ። የምሠራበት ድርጅት በተከታታይ ፕሮጀክቶችን ባለመጨረሱ ምክንያት ፕሮጀክት ማግኘት ስላልቻለ ብዙዎቻችን ከስራ ገበታ ውጪ ሆንን። እኔም ስራ ፈትቼ እያፈላለኩ 5ኛ ወር ያዝኩ ።

በመሃሉ ትልቁ ልጄ ከደረጃ ወድቆ ታሞብኝ ለህክምና ያለኝን ያጠራቀምኩትን ማውጣት ብቻ ሳይሆን ለእለትእለት የምንገለገልበት የገዛዋቸውን ዋጋ የሚያወጡ እቃዎች ሁሉ ሸጬ አሳከምኩት ። እግዚአብሔር ይመስገን ፈጣሪም አየኝ ልጄም ዳነ።

በኋላ ግን ችግር እጦት ቤቴ ውስጥ ከምልህ በላይ ከፋ ። ሰውም ጥሩ ስራ እንደነበረኝ ስለሚያውቅ ችግሬን የሚረዳኝ የለም ። ሰውነቴ ሲታይም በተፈጥሮ ወፍራም ስለሆንኩ የተቸገረ አይመስልም ። እውነታው ግን አንድ ቀን በልቼ አንድ ቀን አንዳች ሳልቀምስ የምውልበት ብዙ ነው ። በእንደዚህ ችግር ውስጥ ብሆንም የምጠይቅህ አንድ ነገር ብቻ ነው ። በተፈጥሮ ብዙም ሰው ለመጠየቅ ድፍረቱም ሞራሉም የለኝም። ወንድ ልጅ ሜዳ ወጥቶ ቸገረኝ ብሎ ሲጠይቅ አያምርምም አሳፋሪም ነው ብዬ እንደምንም ጨክኜ ነበር ። አሁን ግን ቤት ልቀቅ ተባልኩ የቤት ኪራይ ለ3 ወር ባለመክፈሌ ። ቢጨንቀኝ ቀኑ ቢጨልምብኝ እርዳታህን ፈለግኩ ።

ለእኔ ሳይሆን ለልጆቼ ጨነቀኝ ። የት ላድርጋቸው? እባክህ በቻልከው መጠን የአንድ ወር የቤት ኪራዬን አከራዮቼን ለማረጋጋት ከተቻለህ የአንድ ወር እንኳ ብትከፍልልኝ ብዬ ለመጠየቅ መጣሁ ። እባክህ ለኔ ሳይሆን ለልጆቼ ብለህ የአንድ ወር ብቻ ወይም የምትችለውን ሞክርልኝ ። ልለምንህ ከምታመልከው ከአምላክ ታገኘዋለህ … ችግሬን ደፍሬ በመፃፌ ትልቅ ይቅርታም እጠይቃለሁ።

***

አድራሻው አዲስ አበባ አለምባንክ እንደሆነ ገልጾልናል ይህ ወንድማችን ጊዜያዊ የገንዘብ ችግሩን እንዲሁም በተማረበት ሞያ ስራ የሚያገኝበት መንገድ የምታመቻቹ ካላችሁ አድራሻው 0945270063 ነው ማነጋገር ትችላላችሁ።

የንግድ ባንክ አካውንት (ፍፁም ዮሴፍ)
1000081342818





10 comments

Yetkbru Shems Shafi November 7, 2024 - 12:57 pm

ፈጣሪ ከጭንቅህ ያውጣህ

Reply
Sileshe Kbad November 7, 2024 - 12:59 pm

እንባችንም ብስጭታችንም ጭንቀታችን ሁሉ ተሟጦ አልቆ ለምንሰማው ነገር ሁሉ መደነቅ አቆምን ፈዘዝን ደነዘዝን ተራችን የምንጠብቅ ሆን ዋ ለኔ ባይ ሆንን።😭😭😭😭😭😭

Reply
Dagnachew Alemu November 7, 2024 - 1:00 pm

የባንክ ቡክ ቁጥሩንም አያይዘህ በትፖስተው ጥሩ ነበር::የአቅማችንን እንድንረዳው::

Reply
Shame Abdi November 7, 2024 - 1:02 pm

Allah kelabat chiger yaeta

Reply
Meaza Gebre November 7, 2024 - 1:04 pm

Ayzohe wendema egziabher eje yazeregalhal

Reply
የእታገኝ ልጅ November 7, 2024 - 1:10 pm

ወንድሜ ፈጣሪ ከጭንቅ ያውጣህ

Reply
FastMereja.com November 7, 2024 - 1:11 pm

የንግድ ባንክ አካውንት (ፍፁም ዮሴፍ)
1000081342818

Reply
Nafyad Belihun Geleta November 7, 2024 - 1:13 pm

በጣም ያሳዝናል በዉነት :ግን ያልፋል አይዞህ ወንድሜ!

Reply
ማራ ናታ November 7, 2024 - 1:13 pm

ሰው መሆን ድንቅ ተፈጥሮ ነው!!
መልካምነት፣ ቅንነት፣ መረዳዳት፣ ለሌሎች ህልውና መኖር ጥበባዊ ሚስጥር ነው።
ወንድማችንን በቻልን አቅም እንርዳው ነገ እኛ ምን እንደሚገጥመን አናውቅም።

Reply
Ermiyas Chilotaw November 7, 2024 - 1:14 pm

አግዚአብሔር ይርዳሃል ዎንድሜ አይዞህ 🙏

Reply

Leave a Comment