banner

በአዲስ አበባ 17 የሿሿ ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

#FastMereja I በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመንቀሳቀስ የውንብድና እና የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፤ የተለያዩ ንብረቶችም ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ በኤግዚቢትነት ተይዘዋል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው በተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ የሃይል ተግባር በመጠቀም በተለያዩ ግለሰቦች ላይ የቅሚያ እና የውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉ 17 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአድዋ ድልድይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-30785 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ ምሽት ላይ አንድን ግለሰብ ከቦሌ ጌታሁን በሻህ ህንፃ አካባቢ ጭነው ከወሰዱ በኋላ አመቺ ቦታ ሲደርሱ የግለሰቡን እግር በጫማ ገመድ አስረው እና በስለት አስፈራርተው ሞባይል ስልክ እና ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ በአጠቃላይ 21ሺህ 500 ብር የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች ወስደው ተሰውረዋል፡፡

አቤቱታው የደረሰው ፖሊስ ጣቢያው የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ባደረገው ክትትል ወንጀሉ የተፈፀመበትን ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ የወላጆቹ በሆነው ተሽከርካሪ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ ውሎ ምሽት ላይ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ እየተቀበለ መኪናውን አሳልፎ ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ሲሰጥ የነበረ ግለሰብን ጨምሮ በወንጀሉ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 17 ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ ወንጀሉን ሲፈፅሙ የቆዩ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በሌሎች ፖሊስ ጣቢያዎች ተጨማሪ የምርመራ መዝገብ የተደራጀባቸው ስለመሆናቸው ከፖሊስ ጣቢያው የተገኘው መረጃ አመልክቷል ፡፡

34 የተለያዩ አይነት ሞዴል ያላቸው ሞባይል ስልኮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ሌሎች ልዩ ልዩ ንብረቶች በተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ ተገኝተው የምርመራው ስራ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ባለ ንብረቶች የመኪናቸውን ውሎ እና ተግባር ትኩረት ሰጥተው ከመከታተል ባሻገር በአሽከርካሪዎቹ ላይ ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ መሰል ወንጀሎችን ለመከላከል የበኩላቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡





8 comments

ፍቅር ያሸንፋል November 7, 2024 - 2:13 pm

ወይኔ የኔ ስልክም አለ እዚ ውስጥ

Reply
Hayim Ril November 7, 2024 - 2:14 pm

በሰላም መስራት ያልተቻለበት ሀገር 🫤

Reply
Abiti Abiti November 7, 2024 - 2:16 pm

ይዘገያል እንጂ አህያ የጅብ ናት በማርያም አስተማሪ ቅጣት እንጠብቃለን

Reply
Eyob Assefa November 7, 2024 - 2:17 pm

ህጋዊ የሆኑትንስ መቼ ልታሳዮን ነው?🙄

Reply
Degineh Tefo November 7, 2024 - 2:18 pm

ለምንድነዉ ታድያ መንግስት ተደራጅታችሁ ስራን ስሩ የሚሉት ? 🙄

Reply
Bethelihem Assefa Getahun November 7, 2024 - 2:18 pm

በሰላም መስራት የማይቻልበት ሀገር🤧

Reply
ሀብታሙ የሻምበል November 7, 2024 - 2:18 pm

የስራ እድል በዘመድ አዝማድ ሆኖል መስረቅ አስነዋሪ ተግባር ቢሆንም እኔ በርቱ ነው የምላቸው

Reply
Keenboon Sabaa November 7, 2024 - 2:20 pm

Yihe neger beztohal mekinawu biweres tiru yimeslegal

Reply

Leave a Comment