banner

የ14 አመት ታዳጊ ወንድሙን በማገት 1 ሚሊዮን ብር የጠየቀው በእስራት ተቀጣ።

#FastMereja I ተከሳሽ የኔው ብርሀኑ የእንጅባራ ከተማ አሰተዳደር ነዋሪ ሲሆን በጥቅምት 19/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ከቢዳ ጀጎላ ት/ቤት የሚማረውን የ14 ዓመት ወንድሙን ስልክ በመደወል የእናታችንን ልብስ ውሰድ ብሎ ከት/ቤት ከአሰወጣው በኋላ በማገት ከወላጅ ቤተሰቦቹ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን ብር/ መጠየቁን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።

በሁኔታው የተደናገጡት የታጋች ቤተሰቦች ወዲያውኑ ለእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ በሰጡት ጥቆማ በተደረገ ብርቱ ክትትል በሶስተኛው ቀን ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ሲሆን ከተደበቀበት ቢዳጀጎላ ቀበሌ ልዩ ስፍራ አማያስቲ ጎጥ ላይ እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል የላከ ሲሆን መዝገቡ የቀረበለት የአዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ የኔው ብርሃኑ በ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ክፍል ያደረሰን መረጃ ያሳያል።

10 comments

Dagi Jack Adane November 8, 2024 - 6:26 pm

ወዴት ወዴት

Reply
ሚጣ የማርያም ልጅ November 8, 2024 - 6:26 pm

የጉድ ሀገር💔

Reply
Blen Maki November 8, 2024 - 6:26 pm

ይሄ ሚሊዮን ግን የሰው ስም ነው ወይስ…?🙄

Reply
ፍቅሩ የአማረች ልጅ November 8, 2024 - 6:26 pm

ሁለቱም እኮ ናቸዉ የታገቱት😥

Reply
ዘሩ ባቤል November 8, 2024 - 6:26 pm

ገና የማናየውና የማንሰማው ጉድ የለም

Reply
Bereket Dersolign November 8, 2024 - 6:28 pm

አይ ስምንተኛው ሽ (8 ኛው ሺ)

Reply
ሳለአምላክ ነኝ አይናፋሩ November 8, 2024 - 6:28 pm

ይመቸው

Reply
Bekri Mohammed November 8, 2024 - 6:28 pm

ኧረ ፈጠራ 👌😀 ስልጣን ይሰጠዉ

Reply
Hizkiel Jisso November 8, 2024 - 6:30 pm

እግዚኦ!!

Reply
Mekedes Mekdi November 8, 2024 - 6:31 pm

ገና እናታቸውን አግተው ብር ይጠይቃሉ እድሜ ለብልፅግና ምን ያላየነው ያልሰማነው አለ😔

Reply

Leave a Comment