#FastMereja I ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በድህረ-ምረቃ ፣ በቅድመ-ምረቃ፣ በበቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና እና በሰርተፊኬት ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች ለአስራ አንደኛ ዙር ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በወዳጅነት አደባባይ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ::
ዛሬ የተመረቁት በድህረ ምረቃ 343 ተማሪዎች፣ በቅድመ ምረቃ 134፣ በቴክኒክ እና ሙያ 242፣ በሰርተፊኬት 255 በአጠቃላይ 974 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ኮሌጁ እዉቅና ባገኘባቸዉ በድህረ ምረቃ መርሃ-ግብሮች (MSc in International Trade and Economics, MA in Logistics and Supply Chain Management, MBA in Business Leadership, Aviation Management, Strategic Management, Hospitality Management, Banking and Finance, and Risk and Insurance)
በቅድመ ምረቃ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ-ግብር (Aviation Management, Hotel Management, Accounting and Finance and Marketing Management)
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መርሃ ግብሮች (Marketing & Sales Management, Accounting & Finance, Front Office Service እና Hardware & Network Servicing)
በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሺን ባለስልጣን እና ከአለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር International Air Transport Association-IATA ባገኘው ፍቃድ በAirline Cabin Crew, Flight Operation እና Ticketing & Reservation እንዲሁም በርቀት መርሃ ግብር Accounting and Finance, Business Management Marketing Management ፕሮግራሞች ሥልጠና ይሰጣል፡፡
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ የናሽናል ኢንቬስትመንት ግሩፕ አባል እና የናሽናል አየር መንገድ (National Airways) እህት ኩባንያ ሲሆን፣ ሃገራችን በአቪዬሽን፤ በሆቴልና ቱሪዝም እያደገ የመጣዉን የሰለጠነ የሰዉ ኃይል ፍላጎት ከማሟላት አኳያ በሚሰጣቸዉ መርሃግብሮች ብቁ ሙያተኞችን በማፍራት ለዘርፉ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል ተብሏል።
ናሽናል አቭዬሽን ኮሌጅ ከሲቪል አቬሽን ባለስልጣን እውቅና ባገኘበት በአዉሮፕላን ጥገና ቴክኒሽያንነት (Aviation Maintenance Technician) ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን የጀመረ ብቸኛ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው ተብሏል።
ናሽናል አቭዬሽን ኮሌጅ በቅርቡ ናሽናል ዩኒቨርሲቲ የመሆን አላማ ሰንቆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል የተባለ ሲሆን ዘርፎችን በማስፋት በጤናው ዘርፍ በነርሲንግና በፋርማሲ ስልጠና መስጠት መጀመሩን ተገልጿል።





1 comment
አድራሻቸው የት ነው