banner

ልቀት ኮሌጅ የምስረታ በዓሉን በማስመልከት ነፃ የትምህርት እድል ሰጠ።

#FastMereja I ልቀት የኪነጥበብ እና ቢዝነስ ኮሌጅ የተመሰረተበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እስከ ህዳር 10/2017 ዓ.ም ቀድመው ለሚመዘገቡ 200 ተማሪዎች የአንድ ሴሚስተር ከወርሃዊ ክፍያ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ኮሌጁ ህዳር 2 2010 ዓ.ም በአራት ወጣት ባለሞያዎች ተመስርቶ እነሆ አሁን በከተማችን አ.አ ብሎም በሀገሪቱ ትምህርትን በከፍተኛ ጥራት እና ልዩነት እያስተማረ ዛሬ ላለበት ደረጃ ሊደርስ ችሏል።

በተለይም ኮሌጁ በልዩነት በሚታወቅበት የፊልም ትምህርት በከተማችን አዲስ አበባ የፊልም ትምህርትን በብቸኝነት በዲፕሎማ ሲያስተምር ቆይቶ አሁን ደግሞ በሀገራችን ኢትዮጵያ በግል ኮሌጆች ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የፊልም ጥበብ ትምህርትን በመጀመሪያ ዲግሪ በመስጠት ልዩነቱን ከፍ እያደረገ እና ብዙዎችን ከህልማቸው ጋር እያገናኘ ይገኛል።
ልቀት በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው በርካታ ክንዋኔዎች አንዱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በከፍተኛ ቅናሽ በማስተማር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ የቆየ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም ኮሌጁ የተመሰረተበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የመጀመሪያውን ሴሚስተር ወርሃዊ ክፍያ በነጻ የትምህርት እድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ነፃ የትምህርት እድል የተሰጠባቸውም የትምህርት መስኮች:-
ቪዲዮ ካሜራ እና ኤዲቲንግ (Cinematography and Editing)፤
አካውንቲንግ (Accounting and Finance)፤ ማርኬቲንግ (Marketing and sales mangment )፤ የሰው ኃብት አስተዳደር ( Human Resources mangment )፤ የቴአትር ጥበባት ሲሆኑ ምዝገባ ከህዳር 2/2017 እስከ ህዳር 10/2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን የተቋሙ ዲን አቶ መሉጌታ ሙሃመድ ገልፀዋል።

አቶ ሙሉጌታ አክለውም ተመዝጋቢዎች የትምህርት ማስረጃቸውን ዋናውን እና ኮፒ ፣ በተጨማሪም ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዘው በአካል ቀርበው መመዝገብ እንደሚችሉ ገልፀዋል።

ይሄንን ዕድል መጠቀም የሚፈልግ ሁሉ አራት ኪሎ ትምህርት ሚኒስቴር ጀርባ ኢክላስ ህንፃ ላይ በሚገኘው የኮሌጁ ቢሮ በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።



Leave a Comment