banner

«አዲስ አበባን የሐኒሙን ማዕከል እናደርጋለን፣ 1250 ጥንዶች ጥር 18 ይሞሸራሉ»

#FastMereja I ያሜንት ኃ.የተ.የግ. ማህበር ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የየሺህ ጋብቻ ፕሮጀክቶችን እና የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራሞችን ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ 3ኛውን የየሺ ጋብቻ በመጭው ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚያከናውን ተገልጿል።

ዛሬ ሕዳር 05/2017 ዓ.ም በሐርመኒ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በዘንድሮ የየሺህ ጋብቻ 2017 ኪ/ግ ባህላዊ ዳቦ ይጋገራል፣ 12 ሺህ የሚደርሱ የቡና ሲኒዎች ያሉት የቡና እንጠጣ ፕሮግራም ይኖረዋል፣ የሙሽሮች ቁጥር 250 የሚደርሱ ከልዩ ልዩ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ጥንዶች ከ1ሺህ ኢትዮጵያውያን ጥንዶች ጋር በድምሩ 1250 ጥንዶች ወይም በነጠላ 2500 ሰዎች ሰርጋቸውን የሚያደርጉ መሆኑ ተነግሯል።

ያሜንት ኢቬንትስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስናቀ አማኑኤል የየሺህ ጋብቻ ኢኖሚያዊ ፋይዳውን አስመልክቶ ጥንዶች ለሠርግ ድግስ ሊያውሉ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ (በገንዘብ/ንዋይ፤ በጊዜ፣ በጉልበት ወዘተ) በማስቀረት፣ የጥንዶችን ኢኮኖሚ ማጎልበት ለአጠቃላይ አገራዊ ቁጠባ የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ የራሱን ሚና መጫወት ነው ብሏል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦችን የካበተ ባህላዊ የሰርግ ስነ-ሥርዓት አጉልቶ ማሳየት እንዲሁም አዲስ አበባን የሃኒሙን ማዕከል ማድረግ እንደሆነ አቶ አስናቀ ገልጿል።

አጠቃይ ለዚህ ፕሮጀክት ዕውን መሆን ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው በጀት 68,997,500 ብር እንደሆነ ተገልጿል።

የየሺ ጋብቻ ፕሮግራም ያሜንት ኃ.የተ.የግ. ማህበር ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና ከአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባና ደንበኞች አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር እንዲሁም ከሌሎች የፌዴራልና የክልል መንግስታዊ ተቋማት እና ከግል ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ በቅንጅት ይሰራል ተብሏል።





3 comments

Hanni Tesfaye November 14, 2024 - 8:29 am

ጉድ በል ጎንደር

Reply
Teshome Woldesenbet November 14, 2024 - 8:30 am

ጥር ተጋብቶ የካቲት የሚፋቱት ትዳር

Reply
Getachewu Belayineh November 14, 2024 - 8:30 am

ከዛ በአመቱ ይፋታሉ😍

Reply

Leave a Comment