በክልሉ የተከሰተው ተዛማችና ድንበር ተሻጋሪ እየተባሉ ከሚጠሩት ተባዮች ውስጥ አንዱ የሆነው የግሪሳ ወፍ ሲሆን በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ችግር ተደርጎም ይወሰዳል።
በክልሉ በሰሜን ሸዋ፤ በደቡብ ወሎና በኦሮሞ ልዩ ብሄረሰብ ዞኖች የግሪሳ ወፉ እንደተከሰተ የገለጹት የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ፤ ይህን ከአንበጣ መንጋ ጋር የሚመሳሰለውንና አውዳሚ የሆነውን የወፍ ዝርያ በጊዜ ለማጥፋት ክልሉ ከግብርና ሚንስቴር ጋር በመሆን በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል የርጭት ስራ መሰራቱን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡
በዚህም እስካሁን 250 ሄክታር የሚሆን የወፍ ማደሪያ ላይ 501 ሊትር የሚሆን የጸረ ወፍ ኬሚካል በመርጨት ከተከሰተው 29 ሚሊዮን የግሬሳ ወፍ ውስጥ ወደ 16 ሚሊዮን የሚሆነውን ማጥፋት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የተከሰተው ይህ የግሪሳ ወፍ አሁን በተከሰተባቸው ቦታም ሆነ በክልሉ ባሉ ሌሎቹ ዞኖች ጉዳት ሳያደርስ ከወዲሁ ለመቆጣጠር ቢሮው ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን አስፈላጊውን ሁሉ የኬሚካልና የአውሮፕላን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የክልሉ ግብርና ቢሮ በዞን ካሉ የግብርና መምሪያ ባለሙያዎች ጋር በመሆን እስከ ቀበሌ ድረስ የግንኙነት መረብ በመዘርጋት የክትትል ስራውን እንደሚሰራ ዶ/ር ማንደፍሮ አመላክተዋል፡፡
የግሪሳ ወፉ በሌሎችም የክልሉ ዞኖች ተስፋፍቶ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስና እንደ ክልል የታቀደው የምርት መጠን እንዲገኝ የክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ በክልሉ በግሪሳ ወፍ ምክንያት የተከሰተ የሰብል ውድመት ካለ ወደፊት በቢሮው በኩል እንደሚገለጽም አመላክተዋል፡፡
Via: መናኸሪያ ሬዲዮ

10 comments
ፋኖን ጨምሮ ነዉ 😂
29m ወፍ ከመቁጠር ያማራን ችግር መፍታት አይቀልም?
ፋኖ የት ሄዶ?? ቢንቢ ላይ ራሱ አነጣጥረን ነዉ የምንተኩሰዉ አላሉም እንዴ?😂
እንዴት ቆጠራቹሁት
የማን ጥፋት ነው ይሄ
በዚህም ኑሯችን ላይ ግሪሳ 🤨🤨🤨🤨🤨
አለቀላቸው የግሪሳ ወፍ ሳይሆን የአብይ ድሮኖች ናችው 😁
ፋኖ እኮ ናቸው🤣🤣!!
በምን ተቆጠረ
በታምር የተቆጠረው
ጃዊሳ ነው ግርሳ 😂