banner

የ15 ዓመት ታዳጊዋን ለአምስት ሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾ በጽኑ እስራት ተቀጡ

በወላይታ ሶዶ ለአምስት ሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የወረዳው ፍ/ቤት አስታውቋል ።ተከሳሾቹ በቁጥር አምስት ሲሆኑ ጉርዛ ጉቡላ፣ጉቴ ጴጥሮስ፣ሙርቴ ሙኩሎ፣ወጣት ጩምቡሎ ጩጩሞ እና ወጣት ካፍቴ ኢዮና የተባሉ ናቸው፡፡

ግለሰቦቹ በወላይታ ዞን በዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ሻላ ጽጾ ትፌ ቀበሌ ክልል ውስጥ ልዩ ሥሙ ጽጾ ንዑስ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀባቸው ተገልፆል፡፡ የግል ተበዳይ የሆነችው በየነች ሞርካ የተባለች የ15 ዓመት ታዳጊ ስትሆን የጓደኛዋ ሠርግ ቤት ሄዳ ስትመለስ ተከሳሾች ሆን ብለው በቡድን ተደራጅተው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈፀሙባት የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ተከሳሾቹን ፖሊስ በቁጥጥር ስር በማዋል በሰውና በህክምና ሰነድ ማስረጃ አደራጅቶ ለአቃቤ ህግ ያቀርባል፡፡አቃቤ ህግም ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ መነሻ በማድረግ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ በመመስረት ፍ/ቤት ያቀርባል።

በዚህም መሰረት የወረዳዉ ፍርድ ቤት ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት በእያንዳንዳቸው ተከሳሾች ላይ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍ/ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

Via: ዳጉ ጆርናል

10 comments

Abaye Roman November 15, 2024 - 7:58 am

🤔🤔🤔🤔

Reply
Lami G Muse November 15, 2024 - 7:59 am

Demo be Arsenal Jersey 😏 😏

Reply
Endegena Halecha November 15, 2024 - 7:59 am

በጎፋ ዞን

Reply
ካስየ እና ሸዋ November 15, 2024 - 8:00 am

እንዲህ ሲታዩደፋሪ አይመስሉም🙄 እኔኮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መስለውኝ Good Luck ልላቸው ነበር😁

Reply
Mebratu Markos November 15, 2024 - 8:01 am

Ara wolaita wusx indez yemitera woreda yelm merejawun ataru pls

Reply
دانيال ميكونين November 15, 2024 - 8:01 am

አርሰናል 😂 እሄ ዬ አርቴታ ሰራ ነው

Reply
Hagere Gobba Biyya November 15, 2024 - 8:01 am

አፈረድባቸውም ምክንያቱም ምድረሴት ራቆቷዋ መሄድ……

Reply
Tebarek Kersme November 15, 2024 - 8:01 am

ስማቸው ግን ገራሚ ነው

Reply
Den O Zenebe November 15, 2024 - 8:02 am

ወላይታ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ⁉️😂😂😂😂

Reply
Mr-x November 15, 2024 - 8:02 am

ክለባችን Arsenal ምን አለ ባታሰድቡት😭

Reply

Leave a Comment