0
በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡
በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡
የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡
Via: መናኸሪያ ሬዲዮ

10 comments
እቺ ከንቱ አለም ትቶት እንዳኤድ የተደረገው ጥረት ይመቻል
“እኛ ለ 4:00 በጨለማ የቆየነዉ ህይወትን ለማትረፍ ነዉ” ስለተባለ ብቻ ደስ ብሎናል። አይዞን ወገን ነገ ሌላ ቀን ነዉ💪💪💪
ጆን ዳንኤል የስራህን ይስጥህ!!
እንኳን ፈጣሪ አተረፈክ
የኛ ህዝብ በሚያስቅም በማያስቅም ዝብ ብሎ ያሾፋል
ኢትዮጵያዊ መሆኑን በምን እንለይ 🙄😭
እኔም ነገ ንግድ ባንክ ህንፃ ላይ ወጥቼ ጫፍ እዘላለሁ ውረጂ ብላችሁ መለማመጥ የምትፈልጉ ጠዋት 2 ሰአት ኑ 👍 መሮኛል
አፍሪካ ውስጥ ” አልወርድም ” የሚለው ቃል ተወዳጅ ነው።
ታግስ ፣አይዞን ፣ ያልፋል ፣ተስፋ አትቁረጥ
የሚሉህን አትስማቸው ያሰብከውን አሳካ
ነገ ተደብቀኽ ማንም ሳያውቅህ መብራት እያለ ውጣና ያዝ
የኔ ጎበዝ
በጣም ያሳዝናል😭😭😭 ድጋሚ ያስመረረውን ህይወት ሊኖር ነው😭😭😂😂
ይሄማ የወንጌል አማኝ መሆን አለበት ሰው እንዴት ሞቶ ይቆማል የሚገርመው ደሞ ሀይል ማቋረጡ ነው 🙄😭